ግሥላ በእስያ፣ አፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኝ የነብር ዓይነት፣ አጥቢና ሥጋ በል አውሬ ነው። እጅግ ቁጡ አውሬና እልከኛም ነው፡፡
የአንድ ጎልማሳ ግሥላ ክብደት ከ35 እስከ 80 ኪሎ ግራም ሲደርስ፣ ርዝመቱ ከ90 ሴንቲ ሜትር እስከ 1.60 ሜትር ይሆናል፡፡
በአፍሪካ የሚገኘው ዘር እስከ 1.90 ሜትር ይደርሳል፡፡ ከመሬት እስከ ሆዱ ከ50 እስከ 70 ሴንቲ ሜትር ቁመት ሲኖረው፣ ጭራው ደግሞ እስከ 100 ሴንቲ ሜትር ይደርሳል፡፡ ሴቲቱ ከወንዱ አነስ ትላለች፡፡ በዱር እስከ አሥር ዓመት የሚኖር ሲሆን፣ በሰው ተይዞ ሲኖር እስከ 20 ዓመት ይቆያል፡፡