ጢንዚዛ የጉዞ አቅጣጫዋን ለማወቅ ራሷ በምታመነጨው ወተት መሰል ፈሳሽ ትጠቀማለች፡፡ በጉዞዋም የራሷን ክብደት 50 ዕጥፍ የሚሆን የእንስሳት ፍግ ወይም እበትን በመሰብሰብ ማንፏቀቅና መሸከም ትችላለች፡፡
*****
ፓንጎሊን
ፓንጎሊኖች ድንጉጥ የዱር እንስሳ ሲሆኑ ረጅም ምላስ አላቸው፡፡ ምላሳቸውን እንደአፎት ደረታቸው ውስጥ በሚገኘው የደረት ሳጠራ በመመለስና በማስገባት ይጠቀሙበታል፡፡ የልዩ ተሰጥኦ ባለቤት ከመሆን በተጨማሪም የሚታይ ውጫዊ ጆሮ ባይኖራቸውም በደንብ መስማት ይችላሉ፡፡
- ኢዱልጥባ ‹‹ዱር ለዱር›› (2009)