Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [የክቡር ሚኒስትሩ አንድ ወዳጅ ስልክ ደወለላቸው]

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡
  • እንዴ ምን እያሉ ነው?
  • እጅግ ደስ ብሎኛል፡፡
  • ምንድን ነው ደስ ያስባልዎት?
  • ቡድናችን እያሸነፈ ነው፡፡
  • እየተሸነፈ ነው ማለትዎ ነው?
  • ስማ እስካሁን እኮ ምንም ነጥብ አልጣለም፡፡
  • ምንድን ነው የሚያወሩት?
  • ሁሉንም እያሸነፈ ነው፡፡
  • እየፈራረሰ ነው ማለትዎት ነው?
  • አንተ ዲኤስቲቪ የለህም እንዴ?
  • እኔማ የምከታተለው በሶሻል ሚዲያ ነው፡፡
  • ኳሱ ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነው በሶሻል ሚዲያ የሚተላለፈው?
  • የምን ኳስ ነው የሚያወሩት ክቡር ሚኒስትር?
  • የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነዋ፡፡
  • እየቀለዱ መሆን አለበት?
  • የምን ቀልድ ነው?
  • አገሪቷ እንዲህ እየታመሰች ስለ ኳስ ያወራሉ?
  • አየህ ቼክ ኤንድ ባላንስ ያስፈልጋል፡፡
  • የምን ቼክ ኤንድ ባላንስ ነው?
  • ብዙ ስትጨነቅ በዚያው ልክ መዝናናት አለብህ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር መጨረሻዎ ደርሷል ማለት ነው?
  • የማን መጨረሻ?
  • የእርስዎ ነዋ፡፡
  • እኔ መጨረሻ የለኝም፡፡
  • እንደ እግዚአብሔርም ያደርግዎታል?
  • ለሕዝብ እኮ እንደ እግዜሩ ነን፡፡
  • ሕዝቡ ሁሌም የሚለው ይኼንኑ ነው፡፡
  • ምንድን ነው የሚለው?
  • አታዳምጡትም፡፡
  • እኔ የማዳምጠው ሞሪኖን ነው፡፡
  • ምን?
  • እሱ ይሻለኛል፡፡
  • እንዴት?
  • እኛንና ማንችስተርን የሚያመሳስለን ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
  • ምንድን ነው የሚያመሳስላችሁ?
  • አሸናፊዎች ነን፡፡
  • አሁን አይደል እንዴ ማንችስተር ማሸነፍ የጀመረው?
  • ማለት?
  • ይኸው ባለፉት ዓመታት ዝቅተኛ ውጤት ሲያመጣ አልነበር እንዴ?
  • አየህ ዘንድሮ ግን መነሳት ጀምሯል፡፡
  • እና?
  • እኛም ሊወድቁ ነው ሲባል ነው መነሳት የምንጀምረው፡፡
  • ምን?
  • በቃ አሁን እንደ እባብ አፈር ልሰን እንነሳለን፡፡
  • ተስፈኛ ነዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ተስፋማ ወሳኙ ነገር ነው፡፡
  • ወሳኙ ነገርማ ሌላ ነው፡፡
  • ምንድን ነው?
  • ሕዝብን ማድመጥ፡፡
  • ወሳኙማ ማሸነፍ ነው፡፡
  • ሕዝብን ለማሸነፍ ሕዝቡን ማድመጥ ይጠይቃል፡፡
  • ሕዝብን ለማሸነፍ የሚያስፈልገው ሌላ ነው፡፡
  • ምንድን ነው የሚያስፈልገው?
  • ተሃድሶ!

   

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው፡፡
  • የምን አስቸጋሪ ሁኔታ?
  • ሕዝብ በጣም እየተቃወመን ነው፡፡
  • ይኼ እኮ የተለመደ ነው፡፡
  • ይኼኛው ግን የተለመደ ዓይነት አይደለም፡፡
  • ምን የተለየ ነገር አለው?
  • ተቃውሞ ከፍተኛ ነው፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • ይኸው የማራቶን ሯጩ አሸንፎ ተቃወመን እኮ፡፡
  • ቆየ አይደል እንዴ?
  • ኧረ አዲስ ተቃውሞ ነው፤ ሌላ ሯጭ ነው፡፡
  • ድጋሚ?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እና ለእነዚህ ሯጮች ሌላ አሯሯጭ መላክ አለብን ማለት ነው?
  • አሯሯጭ ሲሉ?
  • ፌዴራል ነዋ፡፡
  • እሱ አያዋጣም፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነው የሚያዋጣው?
  • ማዳመጥ፡፡
  • ሕዝቡ የሙዚቃ አልበም አውጥቷል እንዴ?
  • ምን አሉኝ?
  • ወይስ ሕዝቡ ቦብ ማርሊና ቢዮንሴ ሆኗል?
  • ሕዝቡ የተቃውሞ አልበም ነው ያወጣው?
  • እስቲ ዘፈኖቹን ንገረኝ?
  • መልካም አስተዳደር ይስፈን፡፡
  • ሌላስ?
  • ኪራይ ሰብሳቢነት ይወገድ፡፡
  • ቀጥል?
  • ሙሰኞች በሕግ ይጠየቁ፡፡
  • አየህ ሕዝብ ምቀኛ ነው፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • ሌላው ቢሞስን  ምን አገባው?
  • ምን?
  • ኪራይ ቢሰበሰብስ ምን ጨነቀው?
  • እንዴት አይጨንቀው?
  • እኮ ምቀኛ ስለሆነ፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • ከሚመቀኝ ራሱ አይሞስንም፡፡
  • ምን?
  • ከመመቅኘት ኪራይ መሰብሰብ አይሻልም?
  • የእውነትዎትን ነው?
  • እህሳ?
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር አይቀልዱ?
  • እየቀለድኩ አይደለም፡፡
  • የሕዝብ ጥያቄ መመለስ ነው ያለበት፡፡
  • ለመሆኑ ጥያቄው ምንድን ነው?
  • ሰብዓዊ መብት ይከበር፡፡
  • ምን አልከኝ?
  • ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ይኑር፡፡
  • ሌላስ?
  • የሥራ ዕድል ይፈጠርልን፡፡
  • እኔ የምልህ?
  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እኔን ታዲያ ሥራ ያከፋፍላል ያላቸው ማን ነው?
  • ምን?
  • ወይስ ፍትሕ አከፋፋይ ያደረገኝ ማን ነው?
  • መንግሥት መሆንዎትን ረሱ?
  • ለዚያ እኮ ነው ሕዝቡን የምገዛው፡፡
  • ሕዝቡን ለመግዛት ግን ማዳመጥ አለብዎት፡፡
  • ሳላዳምጥም መግዛት እችላለሁ፡፡
  • ይኼማ አምባገነንነት ነው፡፡
  • አምባገነንነት ሳይሆን ሌላ ነው፡፡
  • ሌላ ምን?
  • አምባ ጀግንነት!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር አንድ ዲፕሎማትን ሊያገኙ እየሄዱ ነው]

  • ምን እያደረግክ ነው?
  • እያነበብኩ ነበር፡፡
  • ምንድን ነው የምታነበው?
  • ጉዳችሁን ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የምን ጉድ ነው?
  • በቃ ሁሉንም ጉዳችሁን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ነበር የማነበው፡፡
  • እስቲ መጽሐፉን አሳየኝ?
  • ይኸው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴ? እንዴ? እንዴ?
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ዋናው ፀረ ልማት አንተ ኑረሃል ለካ?
  • ማለት ክቡር ሚኒስትር?
  • ይኼ መጽሐፍ እኮ የተከለከለ መጽሐፍ ነው፡፡
  • ለምንድን ነው የተከለከለው?
  • አንተ ይኼ መጽሐፍ ምን ያደርግልሃል?
  • የሚያደርግልኝንማ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡
  • ይኼ ምንም አይጠቅምህም፤ ሌላ ነገር ብታነብ ይሻልሃል፡፡
  • ሌላ ምን?
  • እንደ አዲስ ራዕይ፣ አዲስ ዘመን፣ አዲስ ልሳን የመሳሰሉትን፡፡
  • ለምን?
  • በቃ አየህ እነዚህን ካነበብክ አስተሳሰብህም አዲስ ይሆናል፡፡
  • ማነው ያለው?
  • ስነግርህ አትሰማም እንዴ?
  • እኔ ክቡር ሚኒስትር የጀመርኩት መጽሐፍ ተመችቶኛል፡፡
  • ነገርኩህ እኮ ይኼን መጽሐፍ ማንበብ አትችልም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ሁሉን ነገር ከልክላችሁት ትችላላችሁ?
  • ምን ተከለከልክ?
  • ሰላማዊ ሠልፍ ከልክላችሁ፣ መጽሐፍ ማንበብ ከልክላችሁ ቀስ ብላችሁ እኮ ሌላም ነገር ልትከለክሉን ትችላላችሁ፡፡
  • ሌላ ምን?
  • ማሰብም ነዋ፡፡
  • እና ሳታስፈቅድ ልታስብ ትፈልጋለህ?
  • እኔስ ምን አልኩ?
  • ለማንኛውም ይኼን መጽሐፍ ማንበብ ስለማትችል፣ አልሰጥህም፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር የማነበውን መምረጥማ መብቴ ነው?
  • ማነው መብትህ ነው ያለው?
  • እናንተው ናችኋ፡፡
  • መቼ ነው እኛ እንደዚህ ነው ያልነው?
  • እንዴ እንደፈለጋችሁ ማሰብ ትችላላችሁ ይላል እኮ ሕገ መንግሥቱ?
  • የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ነው የምትለኝ?
  • አይ ክቡር ሚኒስትር ይኼን እንኳን አያውቁም?
  • ነገርኩህ እኮ፣ የአሜሪካ ሕገ መንግሥት እንደፈለግክ አስብ ሊል ይችላል፡፡
  • የእኛስ?
  • የእኛ ላይማ ካላበድን እንደዚያ አንልም፡፡
  • ኪኪኪ…
  • ምን ያስገለፍጥሃል?
  • ገርመውኝ ነዋ፡፡
  • ምኑ ነው የገረመህ?
  • የእኛም ሕገ መንግሥት ይላል፡፡
  • ከአሜሪካ ስለገለበጥነው ነዋ፡፡
  • መገልበጥማ ማን ብላችሁ፣ ችግራችሁ እኮ…
  • ምንድን ነው?
  • መተግበር!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከዲፕሎማቱ ጋር እያወሩ ነው]

  • በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ናችሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምንድን ነው የሚያሳስበው?
  • አገራችሁ አደገኛ ሁኔታ ላይ ናት፡፡
  • ምን ትሆናለች ብለህ ነው?
  • የሕዝቡን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ካልቻላችሁ አሳሳቢ ነው፡፡
  • እኔን የሚያሳስበኝ የእናንተ አገር ሁኔታ ነው እባክህ?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • እናንተ አገር በርካታ ኢንቨስትመንት አለኝ እኮ፡፡
  • ታዲያ የእኛ አገር ምን ይሆናል ብለው ነው?
  • ስልህ ያንን ሁሉ ኢንቨስትመንት አፍስሼ፣ አንድ ነገር ቢነሳ ያሳስበኛላ?
  • ክቡር ማኒስትር የራስዎት አገር ላይ ቢያተኩር መልካም ነው፡፡
  • ምን እንዳይመጣ ብለህ?
  • በኋላ እንደ ሉሲ እንዳይሆኑ፡፡
  • ሉሲ ምን ሆነች?
  • አልሰሙም እንዴ?
  • ምንም አልሰማሁም፡፡
  • የሞተችው እኮ ወድቃ ነው ተባለ፡፡
  • ከምን ላይ?
  • ከዛፍ ላይ ነዋ፡፡
  • ደግሞ ጦጣ ከዛፍ ላይ ይወድቃላ?
  • ግኝቱ እንግዲህ እሱን ነው ያመለከተው፡፡
  • አሁን በዚያን ጊዜ ማን ኖሮ ነው ከዛፍ ላይ ወደቀች የሚሉት?
  • ሳይንሱ እኮ መጥቋል፡፡
  • ይኼ እባክህ የተላላኪዎቹ ወሬ ነው፡፡
  • የትኞቹ ተላላኪዎች?
  • የሻዕቢያ፡፡
  • ብቻ ያስቡበት፡፡
  • ለመሆኑ እኔና እሷን ምን ያገናኘናል?
  • እርስዎም እንዳይወድቁ፡፡
  • ከምን ላይ?
  • ከሥልጣንዎት!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

  ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

  የአገር ውስጥ የፍራፍሬ ገበያን ፍላጎት ይሸፍናል የተባለለት የብላቴው እርሻ ልማት

  መንግሥት የግብርና ምርታማነትና የፍራፍሬ ምርትን ለማሳደግ በ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በሚል...

  ‹‹ከገበሬው እስከ ሸማቹ ያለውን የንግድ ቅብብሎሽ አመቻቻለሁ›› ያለው ፐርፐዝ ብላክ ውጥኑ ከምን ደረሰ?

  ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚሰማ አንድ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...