Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከሰነድ አልባ ቤቶች ጋር በተገናኘ አምስት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ በምርመራ መለየታቸው ታወቀ

ከሰነድ አልባ ቤቶች ጋር በተገናኘ አምስት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ በምርመራ መለየታቸው ታወቀ

ቀን:

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሃና ማርያም አካካቢ ሰነድ አልባ (ጨረቃ) ቤቶችን ከማፍረስ ጋር በተገናኘ አምስት ሰዎችን በመግደል የተጠረጠሩ በምርምራ መለየታቸው ተጠቆመ፡፡

ቀርሳ ኮንቶማ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ተፈጥሮ በነበረ ግጭት ሁለት የፖሊስ መኮንኖችን የወረዳው ሥራ አስፈጻሚንና ሁለት ነዋሪዎችን በመግደል ተጠርጥረው የታሰሩት ነዋሪዎች ከ200 በላይ እንደነበሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ሕግ ለማስከበር ወደ ሥፍራው የሄዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሁለት መኮንኖችን፣ የወረዳውን ሹምና ነዋሪዎችን ገለዋል ተብለው ተጠርጥረው ከታሰሩት ከ200 በላይ ተጠርጣሪዎች ውስጥ፣ የድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነው የተገኙት ከ40 በላይ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አጣርቶ መጨረሱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ሰምቶና አሰባስቦ በመጨረሱ መዝገቡን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ከአሥር ዓመታት በላይ የኖሩና ውኃ፣ መብራትና መንገድ የገባላቸው መሆኑንም ነዋሪዎቹ በወቅቱ ተናግረዋል፡፡ መንግሥታዊ ተቋማት የነዋሪዎቹን ሕጋዊነት አምነው በሕጋዊ ደረሰኝ የሚያስፈልጓቸውን መሠረተ ልማቶች አሟልተው እያሉ፣ ሕገወጦች መባላቸውና በክረምት ቤቶቹ መፍረሳቸው እንዳሳዘናቸውንም እየገለጹ ነው፡፡

ከአካባቢው አርሶ አደሮች መሬት በመግዛት መታወቂያ አግኘተው ሕጋዊ ነዋሪ ከመሆናቸውም በተጨማሪ፣ የወረዳው ኃላፊዎች ሕጋዊ የቤት ካርታ እንደሚያገኙ በመግለጽ እያንዳንዳቸው ከ2,500 ብር በላይ እንዲከፍሉ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከ20 ሺሕ በላይ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈርሰው ቦታው ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት መሰጠቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...