‹‹የጀርባ ሀቆች›› በየምወድሽ በቀለ የተጻፈ፣ በሴቶች ላይ በተፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ያተኮረ የእውነተኛ ታሪክ ስብስብ መጽሐፍ ነው፡፡ ጸሐፊቷ በመግቢያው እንዳሰፈረችው፣ በለጋ ዕድሜያቸው የቅርብ በሚሏቸው ሰዎች ፆታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች እውነተኛ ታሪክ በመጽሐፉ ተካቷል፡፡ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ከሚደርስባቸው አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እንዲያገግሙ ማድረግ የማኅበረሰቡ ኃላፊነት መሆኑን ታመለክታለች፡፡ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ለማስወገድ ያለሙት 20 እውነተኛ ታሪኮች፣ በ80 ገጽ ተካተዋል፡፡
***
የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ፌስቲቫል
ዝግጅት፡- ባለፈው ሳምንት በተጀመረው ሁለተኛው አዲስ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ፌስቲቫል ቪዲዮዎች እየታዩ ነው፡፡
ቀን፡- ከታኅሣሥ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ 25
ቦታ፡- ብሪትሽ ካውንስል፣ ፈንድቃ የባህል ማዕከል፣ አዲስ ፋይን አርትና ጅማ ጠጅ ቤት
ሰዓት፡- ከ12፡00 ሰዓት ጀምሮ
***
የፊልም ፌስቲቫል
ዝግጅት፡- በ12ኛው ኢትዮጵያን ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል የአገር ውስጥና የውጭ ፊልሞች እየታዩ ነው፡፡
ቀን፡- ከታኅሣሥ 16 እስከ ታኅሣሥ 22
ቦታ፡- ቫድማስ ሲኒማ፣ ፑሽኪንና አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ