Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅቶች በየዓመቱ እስከ 11 ቢሊዮን ብር ለልማት እንዳዋሉ ተገለጸ

የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅቶች በየዓመቱ እስከ 11 ቢሊዮን ብር ለልማት እንዳዋሉ ተገለጸ

ቀን:

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ድርጅት ኅብረት በሥሩ ያቀፋቸው አባል ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበራት ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለኤችአይቪ፣ ለምግብ ዋስትና ለአካባቢ ንፅህና ለመሳሰሉ የልማት ሥራዎች ማከናወኛ በየዓመቱ ከሰባት ቢሊዮን እስከ 11 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጋቸውን አስታወቀ፡፡

የኅብረቱ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበራት የ2008 ዓ.ም. እና የ2009 ዓ.ም. የመልካም ተሞክሮ ቀን በተከናወነበት ሥነ ሥርዓት ላይ የኅብረቱ ዋና ዳይሬክተር መሸሻ ሸዋረጋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ድርጅቶችና ማኅበራቱ ይህን ያህል ገንዘብ ወጪ ያደረጉት ከ2003 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም. ባሉት የበጀት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡

‹‹በአሁኑ ጊዜ ዜጎቻችንን የገጠማቸውን የማኀበራዊ ኢኮኖሚ ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ እኛ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ከመንግሥትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ተቀናጅተን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፤›› ብለዋል፡፡   

የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅቶች ኅብረት ከተቋቋመበት 45 ዓመታት ውስጥ የዜጎችን ማኅበራዊ ኢኮኖሚ ችግሮች ለመፍታት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልጸው፣ በአሁኑ ጊዜ ባወጣው ሁለተኛው የስትራቴጂክ ፕላን ውስጥ አባላቱን በጥራትና በብዛት ለማፍራትና ትኩረት የሚያደርግባቸውን የሥራ ዘርፎች ለማስፋት ማለሙን አስረድተዋል፡፡

መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሀብቶቻቸውን ለተጠቃሚዎች በትክክል ለማድረስ የሚያስችላቸውን የሕግ ማዕቀፍ መንግሥት በማዘጋጀት ላይ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በሚኒስቴር ማዕረግ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ይናገር ደሴ ናቸው፡፡  

ኮሚሽነሩ አያይዘውም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በብሔራዊና በክልል ደረጃ በሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ የዜጎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ፈጠራንና ሐሳብን በማፍለቅ የጎላ ሚና በመጫወት ላይ እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

በኅብረቱ ቅጥር ግቢ ታኅሣሥ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በተከናወነው የመልካም ተሞክሮ ቀን አጋጣሚ በተለያዩ የልማትና የሰብአዊነት ሥራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ 13 ድርጅቶችና ግለሰቦች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ተቀብለዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ሦስቱ በሰብአዊነት ሥራቸው በአንገት የሚጠለቅ የወርቅ ሜዳልያ ሲሸለሙ፣ አንደኛው የጤና አገልግሎት ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ወርቁ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የችግረኛ ሴቶችን ሕይወት በማሻሻል ሥራ ላይ ትኩረት ያደረገውና ‹‹ውመን ኢን ሠልፍ ኸልፕ›› የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት መሥራችና ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽጌ ኃይሉና የቤተሰብ ዕቅድና የሥነ ተዋልዶ ጤና እንዲስፋፋ የላቀ ውጤት ያበረከቱት ወ/ሮ የምሥራች ጥላሁንም የወርቅ ሜዳልያውን አጥልቀዋል፡፡

ሽልማቶቹን የሰጡት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ተቋማቱ የሚያካሂዱት የልማት ሥራን ከብሔራዊና ከክልል የልማት ማዕቀፎች፣ እንዲሁም በመተግበር ላይ ካለው የሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር መቀናጀት እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...