Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርለማን አቤት እንበል

ለማን አቤት እንበል

ቀን:

በኮዬ ፈጬ ኮንደሚኒየም ዕጣ ወጥቶልን ቁልፍ ከተረከብን አንድ ዓመት ከአራት ወራት ሆነን፡፡ ውኃና መብራት ሳይገባልን፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሳይሠራልንና በየደጃፋችን ያለው አፈር ሳይነሳ ተቆልሎ ተቀምጧል፡፡ አንድ ጀሪካን ውኃ አሥር ብር እየዛንና በሻማ እየኖርን ነው፡፡ ከዛሬ ነገ ይስተካከላል በሚል ተስፋ ዓመት አለፈን፡፡ ልጆቻችን እየተሰቃዩ ሲሆን፣ የኑሮ ሁኔታን መቋቋም ያልቻሉ ለሀብታም እየሸጡ ነው፡፡

ዕጣው የዘገየው መሠረተ ልማት እስኪሟላ ነው ይባል ነበር፡፡ ሆኖም ዕጣው ወጥቶ ራሱ ዓመት አልፎን መሠረተ ልማቱ አልተሟላም፡፡ መብራትና ውኃ ሳይገባ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሳይሠራና በየደጃችን የተቆለለው አፈር ሳይነሳ፣ የእፎይታ ጊዜው ተጠናቆ ባንክ ገንዘብ እያስከፈለን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት 900 ሰው ያለበት ዕድርም መሥርተናል፡፡ ወረዳው ጊቢያችን ውስጥ ቢሆንም፣ የእናንተ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ነው እያሉን ይኸው እስካሁን የተጀመረ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ብሶታችንን በማየት ድምፃችንን እንድታሰሙልን በፈጣሪ ስም እንማፀናለን፡፡

(ዓለሙ አበራ፣ ከኮዬ ፈጬ)

*******

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከቁስሉ ሳይሽር በትንሹ አይጥ ሲታመስ

ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት የዕድገት ደረጃ ትልቁ አገራዊ ኃላፊነትን ከሚወጡት መሥሪያ ቤቶች አንዱ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን መሆኑ ሃቅ ነው፡፡ በመሆኑም የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች የትኛውንም የአገሪቱ የአየር ፀባይ ሳይበግራቸው ሌት ተቀን ደፋ ቀና በማለት አገራዊ ግዳጃቸውን እየተወጡ ሲሆን፣ በተለይም ለዘመናት ስንናፍቀው የቆየነውን የዓባይ ግድብን ከግቡ ለማድረስ ያላቸው ተሳትፎ በእጅጉ የላቀ ነው፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ከስንዴ መሀል እንክርዳድ እንዲሉ፣ በቅርቡ በብዙ ቢሊዮን የሚገመት የአገሪቱን አንጡራ ሀብት በማባከን የተጠረጠሩ አንዳንድ የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች በሕግ ጥላ ሥር ሆነው ውሳኔአቸውን እየተጠባበቁ መሆኑ በአገሪቱ የዜና አውታሮች ተገልጿል፡፡

የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሠንጋ ተራ የሚገኘው የዋና መሥሪያ ቤት የቢሮ ጥበቱን ለማቃለል ሁለት ባለ ስድስት ፎቆችን አስገንብቷል፡፡ ይህ ታላቅ መሥሪያ ቤት ከገባበት መዘዝ ሳይላቀቅ የመሥሪያ ቤቱ አንድ የኤሌክትሪክ ሠራተኛ፣ ምንም አገራዊ ኃላፊነት ሳይሰማው አዲሶቹ ፎቆች የገባላቸውን የመብራት ቆጣሪዎች ወይም ብሬከሮች አንድ በአንድ እየቆራረጠ ይወስዳል፡፡ ይህ ክስተት ለረዥም ዓመታት ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ክፍያ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩትን ከ35 ያላነሱ የጥበቃ ሠራተኞች ለእስርና ለእንግልት ዳርጓቸዋል፡፡ ለጊዜውም ቢሆን ከአስር የተረፉትም ቢሆኑ በራሳቸው መተማመናቸውን እንዲያጡና ሥራም እስከመልቀቅ ደርሰዋል፡፡ የታሰሩት የጥበቃ ሠራተኞችም ቢሆኑ ለፖሊስ ምንም እንደማያውቁና ከሙያቸውም ጋር ግንኙነት እንደሌለው ቢገልጹም፣ ከፖሊስ የተሰጣቸው ምላሽ በእርግጥ እናንተ ይህን ድርጊት ልትፈጽሙ ባትችሉም ድርጊቱን የፈጸመውን ይዞ በሕግ የማቅረብ ኃላፊነት ስላለባችሁ ከተጠያቂነት አትተርፉም የሚል ነው፡፡ በእርግጥም የፖሊሶቹ መልስ መቶ በመቶ እውነትነት ያለው ቢሆንም፣ ጥበቃዎቹ በፍተሻ በሚዘዋወሩበት ወቅት ራሱ ዘራፊው አካል እየፈታ እንኳ ቢያገኙት፣ መብራት እየሠራሁ ነው የሚል ምላሽ ስለሚሰጥና ይዞም ሲወጣ በፍተሻ እንዳይገኝበት እዛው መሥሪያ ቤቱ ግምጃ ቤት እያከማቸ በአሳቻ ጊዜ ስለሚያወጣ ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተወዋለን፡፡

(ታዛቢ፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...