Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

አሸንዳ

ቀን:

በሰሜን ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ልጃገረዶች/ሴቶች በተለይ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በወገባቸው ላይ በመቀነቶቻቸው ሸብ አድርገው፣ አስረውና አሸርጠው የሚጫወቱበት ቅጠል አሸንዳ ይባላል፡፡ በ1962 ዓ.ም. የታተመው የአለቃ ደስታ ተክለወልድ ‹‹ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› አሸንዳን ሲፈታው፣ ‹‹ርጥብ ገሣ [ሣር] የትግራይ  ልጃገረዶች በበዓል ቀን ያሸርጡታል›› በማለት ይገልጸዋል፡፡ አሸንዳ በዋግ ኽምራ (ሰቆጣ) በኽምጣኛ ቋንቋ ሻደይ ሲባል፣ ፍችውም ለምለም አረንጓዴ ሣር መሆኑ ይታወሳል፡፡ ዶ/ር ከበደ ታደሰ ባዘጋጁት ‹‹Wild Flowers of Ethiopia – የኢትዮጵያ ወፍ ዘራሽ አበቦች›› መጽሐፍም፣ አሸንዳ (Torch Lily) ረዥም መስመር ቅጠልና ከጫፉ ቢጫ/ቀይ/ብርቱካንማ አበቦች ያለው በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ዓመታዊ ሐመልማል (An endemic herb) ይለዋል፡፡ [ሐመልማል ለምለም ቡቃያ፣ ሣር ቅጠል እንደማለት ነው] አሸንዳ ከ2100 እስከ 4000 ሜትር ከፍታ ላይ በተዳፋትና በመንገድ ዳር ዳር ያድጋል፣ ከሚያዝያ እስከ ጥር ድረስ ያብባል፡፡
 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...