Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልአሸንዳ-ሻደይ አሸንድዬ-ሶላል

አሸንዳ-ሻደይ አሸንድዬ-ሶላል

ቀን:

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙት መቆለ፣ ዓቢይኣዲ፣ ሰቆጣ፣ ላሊበላ፣ ቆቦና ሌሎችም የአካባቢው ከተሞች ነሐሴ አጋማሽ ላይ የከተሜውንም ሆነ yእንግዳውን ቀልብ የሚስቡበት ባህል ነው፡፡ ልጃገረዶች/ሴቶች በነፃነት ነግሠሰው አደባባይ ወጥተው የሚጫወቱበት ልዩ በዓልም አላቸው በክረምት ወቅት ከሚበቅለው የአሸንዳ ተክል ስሙን ወርሷል፡፡ በትግራይ አሸንዳ፣ በሰቆጣ ሻደይ፣ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በቆቦ ሶለል፣ ይሉታል፡፡ ነሐሴ 16 ቀን ከሚከበረው የቅድስት ማርያም በዓል ጋር የተያያዘው ክብረ በዓል ከዋዜማው እስከ ማግሥት ልጃገረዶች የአሸንዳ ቅጠልን አሸርጠው አደባባይ በመውጣትና በየቤቱ በመዞር እየጨፈሩና እያዜሙ የሚያከብሩት በዓል ዘንድሮም በተለያዩ ከተሞች ተከብሯል፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ የበዓሉ መገለጫ በሆኑ አልባሳትና መጋጊያጫዎች ተውበው ታይተዋል፡፡ የፀጉር አሠራራቸው በትግራይ ከአልባሶ እስከ ግልብጭ፣ ከጋመ እስከ ድርብ፤ በሰቆጣም፣ በላሊበላም ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ግልብጭ፣ ሳዱላና ቅርድድ ተሠርተው አደባባይ ውለዋል፡፡ ጌጣ ጌጣቸውም ልዩ ልዩ ዓይነት ሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ፣ መስቀል ሲሆን፣ አለባበሳቸውም በመልጉም /ጥልፍ ቀሚስ/ ፣ ሹፎን፣ ጃርሲ የታጀበ ነበር፡፡ በመGለም ሆነ በሰቆጣ በዓሉ ሲከበር በጋራ የተነሳው ዐቢይ ነጥብ አሸንዳ በዩኒስኮ ወካይ ቅርስነት በዓለም እንዲመዘገብ ጥሪ መቅረቡና ባህልና ተቱሪዝም ሚኒስቴር ድጋፉን እንደሚሰጥ መግለጹ ነው፡፡ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በዓል የውጭ አገር ሴቶች በተለይ የአሜሪካ ሰላም ጓድ (ፒስ ኮር) አባላት የበዓሉ አካል ሆነዋል ያሰኛቸው አልባሳትን አድርገው፣ ፀጉራቸውንም ተሠርተውና በጌጣ ጌጥ ተውበው መታየታቸው ነበር፡፡ ፎቶዎቹ የመGለውን በሮማናት አደባባይ የነበረውን አከባበርና የውጭ ዜጎች ተሳትፎ እንዲሁም የሰቆጣውን ገጽታ ያሳያሉ፡፡ (በሔኖክ ያሬድ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...