Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅስድስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጀርባ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሁሉም እንዳይቀር ሙሉ ማዳበሪያና...

ስድስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጀርባ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሁሉም እንዳይቀር ሙሉ ማዳበሪያና ፍልጥ እንጨት የተጫኑ አህዮች ሲደክመንስ በሚል መልኩ

ቀን:

ላይበቁ ለደቦው

ፎቅ በፎቅ ደረቡ

መርቸዲዝ ተንጋለሉ

በቄሳሩ መዲና ናጠጡ ሸለሉ

ሰርቀው እንዳልከበሩ

ገርፈው እንዳልበሉ

አሰቃይተው ያመለጡ ሁሉ

ተደባለቁን በየሠርጉ

በየስደት ቤቱ

ለሙሾው በየቀብሩ

አልቅሰው ሊያላቅሱን

አብረውን ሊጨፍሩ

ተፅዕኖ ሆነና ያለፈን መወደስ

ወኔ ጠፋና ከህሊና ለመዋቀስ

ንፅህና ደብቦ፣ እውነት እንዳይካስ

መርሳት ልማድ ሆኖ አይከፉት – ክፋት ሲደርስ

እንዳልጋጡን ሁሉ አብረውን ሲበሉ

የተበሉትም ብር ብለው ጨፈሩ

  • ዘበት እልፊቱ ወለሎታት ሰሎሞን ዴሬሳ፣ 1951

የፒዛ ማድረስ አገልግሎት በድሮን

በኒውዚላንድ አንድ የታወቀ ፒዛ ኩባንያ ፒዞዎቹን ደንበኞች ከማፈልጉበት ቦታ በድሮን ሊያደርስ ማቀዱን ሮይተርስ ዘገበ፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎች ምርታቸውን በሞተር አልያም በመኪና ደንበኞች የሚፈልጉበት ቦታ ማድረስ የተለመደ ነገር ነው፡፡ በድሮን ማድረስ ግን ከነአካቴውም በአንድ ወቅት ላይ የማይታሰብም ጭምር ነበር፡፡ በእርግጥ እንደ አማዞን ዶት ኮም፣ ጉግል ወይም አልፋቤት ኢንክ ያሉ የዓለም ትልልቅ ኩባንያዎች አገልግሎታቸውን በድሮን የማድረስ ዕቅድ ነበራቸው፡፡ በአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ያሉ አቬሽኖች በአየር ትራንስፖርት አገልግሎቶችን በማድረስ ረገድ ሕጎቻቸውን ለቀቅ እያደረጉ መሆኑ በዘገባው ተመልክቷለ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ የአሜሪካ ኩባንያ የቡና፣ የዶናትና ዶሮ ሳንዱች የድሮን ደሊቨሪ ሙከራውን አድርጎ ነበር፡፡ የፒዛ የድሮን ደሊቨሪውን ከቀናት በፊት ያደረገው የኒውዚላንዱ ዶሚኖስ ፒዛ ኢንተርፕራይዝ መደበኛ የፒዛ የድሮን ደሊቨሪን በመጀመር ቀዳሚው ኩባንያ የመሆን ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል፡፡

**********

ውሻውን በፕሬዚዳንቱ የሰየመው ተከሰሰ

በናይጄሪያ ውሻውን በፕሬዚዳንት ሙሀማዱ ቡሀሪ የሰየመው ረቡዕ ዕለት ሰዎችን በማስቆጣትና ሰላምን በማደፍረስ የሚል ክስ እንደተመሠረተበት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ግለሰቡ ውሻ ገዝቶ ቡሀሪ ብሎ መሰየሙን እንዲሁም ውሻው ላይ በሁለቱም በኩል ቡሀሪ ብሎ እንደጻፈና በመጨረሻም ይህን ውሻ ይዞ በአደባባይ እንደተንጎራደደ ይህ ነገር የተከሰተበት ከተማ ደቡባዊ ኦጉን ፖሊስ ቃል አቀባይ አቢምቦላ አይይሚ ተናግረዋል፡፡ ግለሰቡ መጀመሪያ በሰዎች ጥቆማ የተያዘ ቢሆንም በመጨረሻ በዋስ ሊለቀቅ ችሏል፡፡ ናይጄሪያ አሁን ካለችበት ያልተረጋጋ ሁኔታ አንጻር የሰውዬው ድርጊት ሰላምን የሚያደፈርስ እንደሆነ ቃል አቀባዩ ለማስረዳት ሞክረዋል፡፡ ናይጄሪያ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በሰሜናዊ ሙስሊሞችና በደቡባዊ ክርስቲያኖች መካከልም በተደጋጋሚ ግጭት ይከሰታል፡፡

************

ፔንጉይን ብርጋዴር ሆነ

በስኮትላንድ ኢደንበርግ ፓርክ ትልልቅ ወታደራዊ አዛዦች ተሰብስበዋል ቦታው ላይ እየተካሄደ ያለው ሥርዓትም የደመቀ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ለአንድ ወፍ የብርጋዴርነት ማዕረግ ለመስጠት ነበር፡፡ በፓርኩ ሰር ኒልስ ኦላቭ እየባለ የሚጠራው ወፍ ነው የብርጋዴርነት ማዕረግ የተሰጠው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...