Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበ281.7 ሚሊዮን ብር ወንጀል የተጠረጠሩ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ኃላፊ ታሰሩ

በ281.7 ሚሊዮን ብር ወንጀል የተጠረጠሩ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ኃላፊ ታሰሩ

ቀን:

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የኢንፖርትና ኤክስፖርት ሥራ አስኪያጅና የውጭ ምንዛሪ መጠን አፅዳቂ ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ብርሃኑ ወልደሰንበት ነገራ፣ ከ281.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡

ግለሰቡ ከተለያዩ አስመጪዎች ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ በመፍቀድ፣ በውጭ ምንዛሪ ላይ ከፍተኛ እጥረት እንዲከሰት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ብርሃኑ ከአስመጪዎቹ ጋር በመመሳጠር የባንኩ አሠራር ከሚፈቅደውና የባንኩ የውጭ ምንዛሪ አፅዳቂ ኮሚቴ የውጭ ምንዛሪ ከፈቀደላቸው አስመጪዎች ውጪ፣ 366 የሚሆኑ ግለሰቦችን ከተፈቀደላቸው ጋር በመቀላቀልና እንደተፈቀደላቸው በማስመሰል 12,544,988 ዶላር (275,362,503 ብር) እና 256,740 ዩሮ (6,359,468 ብር) እንዲጠቀሙ ማድረጋቸውን፣ ነሐሴ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት የፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን በመግለጽ፣ በፌዴራል ፖሊስ መንግሥታዊ ያልሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ