Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ግንባታው በተጠናቀቀው ቦሌ አራብሳ 10/90 ቤቶች የአደጋ መከላከያ ያላደርጉ ሠራተኞች እንዲህ ይሠሩ ነበር

ትኩስ ፅሁፎች

       ፎቶ በታምራት ጌታቸው

የመክሳቴ ሚስጥር

አጥንት ብቻ ሆኜ

ሥጋ በላዬ ቢያጡ፣

ሉኳንዳ ቤት ሄደው

ሙዳ ቀላወጡ፡፡

በኔ ስም ሊበሉ፣

ይኼ ሰው የከሳው፣

ሥጋ አንሶት ነው አሉ፡፡

እኔስ ምኔ ሞኝ ሆኖ

በዝምታ አለፍኳቸው፣

እንዲህ የከሳሁት…

ከጨርቅ የሳሳሁት…

ሆዴን ህሊናዬ

በልጦት ነው አልኳቸው፡፡

  • እርቅይሁን በላይነህ ‹‹እርቃንሽን ቅሪ›› (2007)

* * *

40 ቢላዎች በቀዶ ሕክምና የወጡለት ሰው

በህንድ አምሪስታር በተሰኘ ከተማ አንድ የ42 ዓመት ጐልማሳ በሁለት ወራት ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑ ቢላዎችን መዋጡን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡ የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፖሊስ ሆዱን በተሰማው ከፍተኛ ህመም ምክንያት ወደ ሆስፒታል ሄዶ በተደረገለት የአምስት ሰዓት ቀዶ ሕክምና 40 ቢላዎች ከሆዱ ወጥተውለታል፡፡ ግለሰቡ ‹‹ለምን እንደዚያ እንዳደረግኩኝ አላውቅም፡፡ ነገር ግን አንዳች መንፈስ ከድርጊቴ ጀርባ አለ፤›› ብሏል፡፡ ግለሰቡ እንዳለው ከሁለት ወራት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ቢላ ሲውጥ ደስ የሚል ስሜት አድሮበታል፡፡ ሐኪሞች መጀመሪያ የግለሰቡ የጤና ችግር ዕጢ ነው ብለው የጠረጠሩ ቢሆንም በሲቲስካን ሆዱ ውስጥ የተከማቹ ብዙ ጠጣር ነገሮች መኖራቸውን ሊያውቁ ችለዋል፡፡ ቀጥሎ ባደረጉት ተጨማሪ ምርመራም እስከ 18 ሴንቲ ሜትር ርዝመትና የብረትና የእንጨት እጀታ ያላቸው ቢላዎች ከበሽተኛው ሆድ ውስጥ መኖራቸውን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

* * *

ጀርመኖች ለአሥር ቀን የሚሆናቸውን ምግብና ውኃ በቤታቸው እንዲያኖሩ ተነገራቸው

የሽብር ጥቃት ወይም ተፈጥሮአዊ አደጋን ታሳቢ በማድረግ ዜጐች ለአሥር ቀናት የሚሆናቸውን ምግብና የአምስት ቀን ውኃ በቤታቸው እንዲያከማቹ የጀርመን መንግሥት ለዜጐች ሊያሳውቅ መሆኑን አንድ የአገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መንግሥት ዜጐች ለአሥር ቀን ምግብ ለአምስት ቀን የሚሆን ውኃ እንዲያስቀምጡ ብቻም አይደለም ያደረገው፡፡ በፖሊስና በፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም የሳይበር ወንጀልን መዋጋት ላይ ኢንቨስት እያደረገ ነው፡፡ ባለፈው ወር የአዕምሮ ችግር ያለበት ታዳጊ ሰዎች ላይ ጥይት ካርከፈከፈ በኋላ ጀርመን ከፍተኛ የፀጥታ ማስጠንቀቂያ ውስጥ መሆኗ ይታወቃል፡፡

አባት በደንብ አላጠናም ያለውን ልጁን ገደለ

በጃፓን ጥሩ ከሚባሉት ትምህርት ቤቶች ለመግባት ያለው ውድድር ከፍተኛ ነው፡፡ ትልቅ ግምት ከሚሰጣቸው ትምህርት ቤቶች ልጆችን ማስገባትም የልጆችን የወደፊት ስኬት እንደማመቻቸት ይቆጠራል፡፡ በጃፓን አንድ ከተማ ውስጥ ጥሩ ትምህርት ቤት ለመግባት የሚያስችለውን ፈተና ያልፍ ዘንድ በደንብ አላጠናም ያለውን ልጁን አባት በቢላ ወግቶ መግደሉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በምግብ ቢላ ደረቱ ላይ የተወጋው ሪዎታ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ብዙ ደም ስለፈወሰው ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ አባት ልጁን የወጋው በስህተት መሆኑን ቢናገርም የሕፃኑ ሕይወት እንዳለፈ ወዲያው በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል፡፡ ሕፃኑ በከተማው አሉ ከሚባሉት የግል ትምህርት ቤቶች ከአንዱ ለመግባት ተፈትኖ እንደነበር፤ አደጋው በደረሰ ወቅትም እናት ከቤት እንዳልነበረች በዘገባው ተመልክቷል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች