Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአገልጋይነት ባህሪ የተላበሰ የጤና ባለሙያ ከማፍራት አኳያ ብዙ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

የአገልጋይነት ባህሪ የተላበሰ የጤና ባለሙያ ከማፍራት አኳያ ብዙ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

ቀን:

ከጤና አገልግሎት ጥራት፣ ፍትሃዊነትና ተደራሽነት፣ የማኅበረሰቡን ተሳትፎ ከማረጋገጥና የባለቤትነት መንፈስ ከመፍጠር እንዲሁም አዛኝ፣ ሩህሩህ፣ አክብሮት የተሞላበትና የአገልጋይነት ባህሪ የተላበሰ የጤና ባለሙያ ከመፍጠር አኳያ ብዙ መሥራት እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ አስታወቁ፡፡

ነሐሴ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር በካፒታል ሆቴል ባካሄደው የወርቅ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል ላይ ፕሬዚዳንቱ እንደገለጹት፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እነዚህን አበይት ጉዳዮች በተሳካ መልኩ ለመተግበር ሰፊና በርካታ ግቦች ተቀምጠዋል፡፡

በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት በተደረገው ጥረትም ውጤት መመዝገቡን፣ ከወሊድ ጋር በተያያዘ የእናቶችን ሞት በ72 በመቶ መቀነስ መቻሉን፣ ከአንድ ዓመት በታች የሚሞቱ ሕፃናት ቁጥርን በ23 በመቶ፣ ከአምስት ዓመት በታች የሚሞቱ ሕፃናትን ደግሞ በ67 በመቶ መቀነሱን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አንፃር እጅግ ዝቅተኛ የነበረውን የአንድ ሰው አማካይ በሕይወት የመኖር ዕድሜ ጣሪያን 64 ዓመት ለማድረስ እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት በ1982 ዓ.ም. ከነበረበት ሦስት በመቶ በ2007 ዓ.ም. ወደ 42 በመቶ ከፍ በማድረግ አንድ እናት በሕይወት ዘመኗ የምትወልዳቸው አማካይ የልጆች ቁጥር ከ7.7 ወደ 4.1 ዝቅ እንዲል መደረጉን ዶ/ር ሙላቱ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ከበደ ወርቁ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ በአፍላ ወጣትነት ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭ ስለሆኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶች ጤና አገልግሎትን ለማስፋፋት መሠረታዊ የአገልግሎት ፓኬጅ የያዘ ብሔራዊ ስትራቴጂ መቅረፁን፣ በማስተግበሩ ረገድ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ወይዘሮ መዓዛ ቅጣው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር ፕሬዚዳንት ‹‹ማኅበሩ የግማሽ ምዕተ ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ የሚሆነው በጀቱን የሚያገኘው ከውጭ ለጋሾች ነው፡፡ ዳሩ ግን በአሁኑ ወቅት የለጋሾች ዕርዳታ በልዩ ልዩ ምክንየት እየቀነሰ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተዋልዶ ጤና አገልግሎቱን አጠናክሮ የመቀጠልና በስትራቴጂክ ዕቅዱ የስቀመጣቸውን ዋና፣ ዋና ግቦች ለማስፈጸም ሌሎች አማራጮችን መፈለግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ በዕቅዱ ላይ ተመልክቷል፤›› ብለዋል፡፡

ከአማራጮችም መካከል ዋና ዋናዎቹ ከመንግሥት የሚያገኘውን የማቴሪያልና የገንዘብ ድጋፍ ማጠናከር የሚችልበት ሁኔታ ላይ መሥራት፣ የራሱ ገቢ እንዲኖረው ጥረት ማድረግ፣ ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ገንዘብ ማሰባሰብና የበጎ ፈቃደኞችን ድጋፍ ማጠናከር የሚሉ እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡

የአገሪቱ ቢዝነስ ኮሚቴ አላባትም የማኅበራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ፣ በሌሎች አገሮች አንደሚታየው የሶሻል ኮርፖሬት ፈንድ በማቋቋም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወጣት ጽዮን በላይ የብልህ ወጣቶች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለጤና ሰብሳቢና ፕሬዚዳንት ከአሥር እስከ 24 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊ አፍላዎችና ወጣቶች ባለፉት ሁለት ዓመታት በድምሩ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን ልዩ ልዩ የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መስጠቱን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...