‹‹መንግሥት የተፈጠረውን ሁከት ለማረጋጋት ከታዋቂ ሰዎችና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር እየሠራ ነው››
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ለሆነ የእስያና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች አምባሳደሮች ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ አምባሳደር ታዬ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ሁከቶች ሕዝቡ ለሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች የመንግሥት ምላሽ በመዘግየቱ ነው ብለዋል፡፡ አምባሳደሮቹ በሁከቶቹ ምክንያት ለደረሰው ጉዳት እየተደረገ ስላለው ማጣራት ላቀረቡት ጥያቄ፣ መንግሥት ያለምንም ጣልቃ ገብነት ማጣራት የሚያደርግ አካል መመደቡን ተናግረዋል፡፡ በምሥሉ የሚታዩት አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ናቸው፡፡