Wednesday, October 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ኦሞ ኩራዝ ሁለት የስኳር ፋብሪካ ምርት ማምረት መጀመሩ ታወቀ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ከ667 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣነት የተገለጸው የኦሞ ኩራዝ ሁለት የስኳር ፋብሪካ ምርት መጀመሩ ተገለጸ፡፡ ለፋብሪካው ግንባታ የወጣው ወጪ ከቻይና ልማት ባንክ የተገኘ ብድር ነው፡፡

   

  የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን እንደገለጸው ባለፈው ዓመት ፋብሪካው የምርት ሙከራ ጀምሮ ባልተጠበቀ ዝናብ ምክንያት ቢቋረጥም፣ አሁን ከታህሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ምርት ማምረት እንደጀመረ የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክት አቶ ጋሻው አይችሉህም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

   

  ፋብሪካው ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባ ሲሆን፣ በቀን 12 ሺሕ ቶን ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት አቅም አለው፡፡ የፋብሪካው የማምረት አቅም 2.5 ሚሊዮን ቶን እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

  አሁን ላይ ፋብሪካው በግማሽ አቅሙ እያመረተ መሆኑ ታውቋል፡፡

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -