Tuesday, March 5, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅፋና ወጊው አበበ ቢቂላ

ፋና ወጊው አበበ ቢቂላ

ቀን:

ጳጉሜን 5 ቀን 1952 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዋዜማ አበበ ቢቂላ ታሪክ ሠራ፡፡ በማራቶን ባዶ እግሩን ሮጦ በጊዜው የዓለም ሬኮርድ በነበረ በ2 ሰዓት 15 ደቂቃ 16.2 ሴኮንድ በማሸነፍ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያና የነፃ አፍሪካ አገር ወርቅ ሜዳልያ አገኘ፡፡ አበበ ዋቅጅራ ሰባተኛ ወጣ፡፡ የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ድሎችም በዚህች ልዩ ቀንና በዚህ ታሪካዊ አትሌት ተጀመሩ፡፡

አበበ ቢቂላ መስከረም 5 ቀን 1953 ዓ.ም. አዲስ አበባ ሲገባ ብዙ ሺ ሕዝብ በድሮ አይሮፕላን ማረፊያና በሚያልፍበት መንገድ ደማቅ አቀባበል አደረገለት፡፡ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሆነው ገነተ ልዑል ቤተመንግሥታቸው ተቀብለው የኢትዮጵያ የፈረሰኛ ኮከብ ኒሻን ሸለሙት፡፡

ፓሪ ማች የተባለውን ታዋቂ የፈረንሣይ መጽሔት ጨምሮ ኢንተርናሽናል ጋዜጦች ወኪሎቻቸውን አስቀድመው ወደ አዲስ አበባ ልከው ስለነበር የተመለከቱትን በአድናቆት ለዓለም አሠራጩ፡፡ ፎቶዎቹ ከ56 ዓመት በፊት ለአበበ ቢቂላ የተደረገለትን የጀግና አቀባበል ያሳያሉ፡፡ (ከይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ ድረ ገጽ የተወሰደ)

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

***

ጠብቄሽ ነበረ

ጠብቄሽ ነበረ
መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ፡፡
                – ደበበ ሰይፉ ‹‹ለራስ የተጻፈ ደብዳቤ›› (1992)

***

የፊደል ካስትሮን 90ኛ ዓመት አስመልክቶ 90 ሜትር ሲጋራ ተዘጋጀ

የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ባሳለፍነው ሳምንት ማብቂያ ያከበሩትን 90ኛ ዓመት አስመልክቶ፣ 90 ሜትር ርዝመት ያለው ሲጋራ ተሠራ፡፡

ሲጋራ አምራቹ ጆሲ ካስትለርና የሥራ ባልደረቦቹ፣ 90 ሜትሩን ሲጋራ ለመሥራት፣ 10 ቀናት የፈጀባቸው ሲሆን፣ ሠራተኞቹም በየቀኑ ለ12 ሰዓታት መሥራታቸውን ካስትለር ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ገልጿል፡፡

ካስትሮ፣ እ.ኤ.አ. ከ1980 ወዲህ ሲጋራ አጭሰው አያውቁም፡፡ ‹‹ለዚህ ውሳኔ የደረስኩት ሲጋራ በኅብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለማሳየትና ለኩባ ሕዝብ ስል የከፈልኩት መስዋዕትነት ነው፡፡ ሆኖም እንዳጣሁት አይሰማኝም›› ብለዋል፡፡

በአጫሽነታቸው የሚታወቁት ካስትሮ ማጨስ ካቆሙ ዓመታት ቢያስቆጥሩም፣ ሲጋራ አምራቾቹ ለካስትሮ  ያላቸውን ክብር ለመግለጽ፣ ሲጋራውን ሠርተው፣ በካስትሮ የልደት ቀን በስጦታ አቅርበዋል፡፡ ለካስትሮ የእንኳን አደረሰህ የልደት መልዕክትም በገፍ መድረሱን ዘገባው ያሳያል፡፡

***

በአውሮፕላን ውስጥ የቀረበ የጋብቻ ጥያቄ በሠርግ ተጠናቀቀ

በረራቸውን ወደ አቴንስ ያደረጉት ለመዝናናት ነበር፡፡ ሆኖም በቬና እና በግሪክ መካከል እያሉ ቀያይ የለበሱ ሰዎች በግራና በቀኝ ሆነው ምርጥ ዜማ ማንቆርቆር ጀመሩ፡፡ ናታሊ ኢቼ ለአንዷ ሴት የጋብቻ ጥያቄ ይኖራል ብላ ነበር ያሰበችው፡፡ ሆኖም አንገቷን ወደኋላ ስታዞር የተመለከተችው የወንድ ጓደኛዋን ጀርገን ቦንገርን ነበር፡፡

‹‹ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ እሱም ተንበርክኮ እንዳገባው ጠየቀኝ›› ስትል ለኤንቢሲ ገልጻለች፡፡ በቀጣይም የሙሽራ ልብስ፣ ሁለት ቀለበት እንዲሁም የቫዮሊን ተጫዋች፣ የሠርግ ሥነ ሥርዓት አቀናባሪ በኢቼ ፊት ቀረቡ፡፡ እንደዘገባው ከሆነ፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ ኢቼ ሳትመለከታቸው የተሳፈሩና ሠርጉን የሚያጅቡ ቤተሰቦቻቸው ነበሩ፡፡

አባቷ ለኢቼ የአበባ እቅፍ ካበረከቱት አንዱ ነበሩ፡፡ ‹‹የጋብቻ ጥያቄውን እንደምቀበለው ቦንገር ያውቅ ነበር፡፡ እናም በተመሳሳይ በረራ ላይ ጥያቄውም ጋብቻውም ተፈጽሟል›› ብላለች፡፡

***

ዝሆኗ የወረወረችው ድንጋይ አንዲት ሕፃን ገደለ

በሞሮኮ በሚገኘው የእንስሳት ማቆያ ውስጥ እንስሳት በመጐብኘት ላይ ከነበሩ ቤተሰቦች መካከል የ7 ዓመቷ ሕፃን በሴት ዝሆን በተወረወረባት ድንጋይ ሕይወቷ አለፈ፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ሕፃኗ ከቤተሰቦቿ ጋር በመሆን ሦስት ዝሆኖች ያሉበትን ስፍራ እየጐበኘች ነበር፡፡ በመሃሉም አንዷ ዝሆን ድንጋይ አንስታ ትወረውራለች፡፡ ድንጋዩ ያረፈው ሕፃኗ ጭንቅላት ላይ ነበር፡፡

በሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት በሚገኘው የእንስሳት ማቆያ፣ የእንስሳት ሐኪም የሆኑት አብድራሂም ሳልሂ፣ ‹‹ዝሆኗ ደስተኛ አልነበረችም፡፡ ይህንን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የማንኛውም እንስሳ ባህሪ ተቀያያሪና ለመረዳት የሚያስቸግር ነው፡፡ በተለይ የዱር እንስሳት ባህሪን ለመተንበይ ያስቸግራል፡፡ እኛም የዝሆኗ ሁኔታ ገርሞናል፡፡ ግልፅም አልሆነልንም›› ብለዋል፡፡ የእንስሳት ማቆያው በሕፃኗ መሞት ለሦስት ቀናት ያህል ከተዘጋ በኋላ ለጐብኚዎች ዳግም ክፍት ሆኗል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...