Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  አዲስ ንግድ ለዕድገት ባዛር ላይ 350 ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በርካታ ጐብኚዎች እንደሚገኙባቸውና ከፍተኛ ግብይት እንደሚካሁዱባቸው ከሚታመንባቸው የበዓላት የዋዜማ ንግድ ትርዒቶችና ባዛሮች መካከል አዲስ ንግድ ለዕድገት የንግድ ትርዒት አንዱ ነው፡፡

  ለ23 ቀናት የሚቆየውና ሰሞኑን የተከፈተው የንግድ ትርዒት ላይ ከ350 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሲሆኑ፣ ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ከማስተዋወቅ ሌላ ምረቶቻቸውን ለገበያ ያወጣሉ ተብሏል፡፡  

  በንግድ ትርዒት ዝግጅት ከ16 ዓመታት በላይ በቆየው ሴንቸሪ ፕሮሞሽን አማካይነት የተዘጋጀው 25ኛው አዲስ ንግድ ለዕድገት የንግድ ትርዒትና የአዲስ ዓመት ፌስቲቫል ላይ ከሕንድ፣ ከኬንያ፣ ከሱዳን፣ ከናይጄሪያና ከሶርያ የተጋበዙ ኩባንያዎች ታድመዋል፡፡

  ከሴንቸሪ ፕሮሞሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በንግድ ትርዒቱ ላይ ከሚሳተፉ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቂያነት እስከ 30 በመቶ ቅናሽ በማድረግ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡

  ከተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ጋር እየተዋዙ የበዓላት ዋዜማዎችን ታከው ከሚዘጋጁ የንግድ ትርዒቶችና ባዛሮች መካከል በአዲስ ዓመት ዋዜማ ወቅት የሚዘጋጁ የንግድ ትዒርቶች ከፍተኛ ጎብኚዎችን በማስተናገድ ይታወቃሉ፡፡

  ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ባሻገር ከፍተኛ የጎብኚዎች ቁጥር የሚያስተናግዱት በፋሲካና በገና በዓላማ ዋዜማ የሚዘጋጁት የንግድ ትርዒቶችና ባዛሮች ናቸው፡፡

  በእነዚህ በዓላት ወቅት በቀን ከ20 እስከ 40 ሺሕ ጎብኚዎች እንደሚስተናገዱና እንደሚጎበኙ ይገለጻል፡፡ ይህ በመሆኑም እንዲህ ያሉትን በዓላት መነሻ በማድረግ የንግድ ትርዒት አለያም ባዛር ለማዘጋጀት የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል፡፡ የዘንድሮውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ሴንቼሪ ፕሮሞሽን ለማዘጋጀት የቻለው ባቀረበው የ8.7 ሚሊዮን ብር ዋጋ አሸናፊ በመሆኑ ነው፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች