Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወጣቶች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ተራዘመ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወጣቶች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ተራዘመ

ቀን:

ነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና በወጣቶች መካከል ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞ የነበረው ውይይት ለሁለት ሳምንት ተራዘመ፡፡

‹‹ነሐሴ 13 እና 14 ቀን 2008 ዓ.ም. አገር አቀፍ የወጣቶች የንቅናቄ ተሳትፎ ኮንፈረንስ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለባቸው ተደራራቢ የሥራ ጫና ምክንያት በዕለቱ ሊመቻቸው ስላልቻለ ውይይቱ ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲካሄድ ተወስኗል፤›› ሲሉ በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ እንየው ዓሊ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ መራዘም በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ይገናኝ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹አሁን በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ቀደም ሲል በተሰጠው መግለጫ መሠረት ወጣቶቹ ነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ከተለያዩ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ነሐሴ 14 ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወጣቶቹ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ተገልጾ ነበር፡፡ አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላልተመቻቸውና ተደራራቢ ሥራ ስላለባቸው ብቻ ተራዘመ እንጂ፣ ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፤›› በማለት አቶ እንየው አስረድተዋል፡፡

ውይይቱ ከወጣቶች ፖሊሲ ላይ ከታቀዱ ዋና ዋና የልማት ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ውስጥ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ምን ደረጃ ላይ ደርሷል? ስኬቶቹ ምንድናቸው? ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ምን ይመስላሉ? ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ምን መሆን አለባቸው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...