Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊደካማ ሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰፋፊ የእርሻ ፕሮጀክቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

ደካማ ሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰፋፊ የእርሻ ፕሮጀክቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

ቀን:

በሰፋፊ እርሻ ልማቶች መሬት ወስደው በውላቸው መሠረት ወደ ሥራ ላልገቡ ዘጠኝ ኩባንያዎች የመጀመርያና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ፡፡

የግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ መሬት የተሰጣቸው ኩባንያዎችን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ በገቡት ውል መሠረት ሥራቸውን አልሠሩም የተባሉት ኩባንያዎች መካከል፣ የቱርክ ኩባንያ የሆኑት አይካ አዲስና አሞቫሊና አወዛጋቢው የህንድ ኩባንያ ቬርዳንታ ሐርቨስት ይገኙበታል፡፡ በአጠቃላይ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ዘጠኙ ኩባንያዎች በደቡብ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች መሬት የወሰዱ ናቸው፡፡

ግዙፉ የቱርክ የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ አይካ አዲስ በኦሮሚያ ክልል ሰበታ አካባቢ ለገነባው ፋብሪካ ጥሬ ዕቃ የሚሆን ጥጥ ለማምረት በደቡብ ክልል 10,000 ሔክታር መሬት ተረክቦ ነበር፡፡

ነገር ግን ኤጀንሲው ባካሄደው ግምገማ ኩባንያው በ2006 ዓ.ም. በወሰደው መሬት ምንም ዓይነት ልማት ባለማካሄዱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው ታውቋል፡፡

ሌላኛው የቱርክ ኩባንያ አሞቫሊ በደቡብ ክልል በ2004 ዓ.ም. 10,000 ሔክታር መሬት ለጥጥ ልማት ተረክቦ ነበር፡፡ ነገር ግን እስካሁን 8,000 ሔክታር መሬት ማልማት ያለበት ቢሆንም፣ ማልማት የቻለው 1,120 ሔክታር መሬት ብቻ በመሆኑ የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡

አወዛጋቢው የህንድ የሻይ ቅጠል ኩባንያ ቬርዳንታ ሐርቨስት በ2002 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን 3,012 ሔክታር መሬት ተሰጥቶታል፡፡ ኩባንያው እስካሁን 1,807.2 ሔክታር መሬት ማልማት ቢኖርበትም ማልማት የቻለው ግን 143.5 ሔክታር መሬት ብቻ ነው፡፡

ቬርዳንታ መሬት የወሰደው የበርካታ ወንዞች መነሻ በሆነ ተራራማ ሥፍራ ነው፡፡ ተራራው ደግሞ በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነ በመሆኑ ኩባንያው ልማቱን የሚያካሂደው ደን እየጨፈጨፈ በመሆኑ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ሲወዛገብ መቆየቱን ሪፖርተር ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይህ ኩባንያ የአካባቢውን ማኅብረሰብ ድጋፍ ማግኘት ያልቻለ ቢሆንም፣ ዕርምጃ የተወሰደበት በሥራ አፈጻጸሙ ደካማነት ብቻ ኤጀንሲው የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ዮሜድ አግሪካልቸራል፣ ጉጠት፣ ዶ/ር ጣዕመ ሐድጉ፣ ዳሰነች አግሮ ዴቨሎፕመንት፣ ዳሰሊ እርሻ ልማትና ኦቶማን ኢሳ አግሮ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡

የግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዘነበ ለሪፖተር እንደገለጹት፣ ኤጀንሲው ባካሄደው ግምገማ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው ኩባንያዎች ውጥ አምስቱ በደቡብ፣ ሦስቱ በቤንሻንጉልና አንዱ በጋምቤላ ክልሎች የሚገኙ ናቸው፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ወደ ሥራ መግባት እንደሚኖርባቸው በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ እንደተገለጸላቸው አቶ ዳንኤል አስረድተዋል፡፡

የግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ከጥር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሰፋፊ እርሻዎች መሬት መስጠት አቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም የሰጠው መሬት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በማጥናት ላይ ሲሆን፣ በ2009 ዓ.ም. መሬት እንደሚያቀርብ የተሰጠ ማረጋገጫ የለም፡፡

ኤጀንሲው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለህንዱ ግዙፍ ኩባንያ ካሩቱሪ የሰጠውን መሬት መንጠቁን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...