Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ስምንት ተከሳሾች በነፃ ተሰናበቱ

ከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ስምንት ተከሳሾች በነፃ ተሰናበቱ

ቀን:

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለሕዝብ ውኃ ለማቅረብ በውጭ ምንዛሪ ያስገባቸውን ከ8.2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 120 ዓይነት የቧንቧ ዕቃዎች፣ በሕገወጥ መንገድ በመውሰድ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ተከሰው ከነበሩት አሥር ተጠርጣሪዎች ውስጥ ስምንቱ በነፃ ተሰናበቱ፡፡

በነፃ የተሰናበቱት ተጠርጣሪዎች አቶ ተሾመ አበበና አቶ ጎርፉ ጠንክር (የባለሥልጣኑ የጥበቃ ሠራተኞች)፣ በግል ሥራ የሚተዳደሩት አቶ ተሻለ ገላን፣ አቶ ቡርቃ ሙለታ፣ አቶ ማንደፍሮ ጌታቸው፣ አቶ ሲሳይ ሳህሌ፣ አቶ መኮንን ተመስገንና አቶ መስፍን ይትባረክ ናቸው፡፡

ከአቶ መስፍን ይትባረክ፣ ከአቶ ተሾመ አበበና ከአቶ ጥላሁን ታደሰ በስተቀር፣ ሌሎቹ ተከሳሾች ጉዳያቸው ሲታይ የከረመው በሌሉበት መሆኑን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ብይን ይገልጻል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ጥላሁን ታደሰ ከባለሥልጣኑ ዕቃዎች ውስጥ ግምታቸው 1,457,120 ብር የሆኑ የቧንቧ ዕቃዎች በመጋዘናቸው ውስጥ ሸሽገው መገኘታቸውን፣ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ስላስረዳባቸው እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ አቶ አብዮት ከድር የተባሉት ተከሳሽ ደግሞ ጉዳያቸው በሌሉበት መታየቱን ፍርድ ቤቱ ገልጾ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

በሌሎቹ ተከሳሾች ላይ ዓቃቤ ሕግ ድርጊቱን ስለመፈጸማቸው የሚያስረዳ የሰውም ሆነ የሰነድ ምስክሮችን (ማስረጃዎችን) ስላላቀረበባቸው፣ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጥላሁን ታደሰ መከላከያ ምስክሮቻቸውን እንዲያቀርቡ ለየካቲት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በአቶ አብዮት ከድር ላይ ደግሞ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ አቶ መስፍን ይትባረክ፣ አቶ ቡርቃ ሙላትና አቶ ተሾመ አበበ በዕለቱ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከጥበቃ ሠራተኞች ጋር በመመሳጠር ባለሥልጣኑ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግምጃ ቤት ውስጥ 120 ዓይነት የቧንቧ ዕቃዎችን ወስደዋል በማለት፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...