Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትግብፃዊው ክስተት

ግብፃዊው ክስተት

ቀን:

አጭሩ ታክቲከኛ በእንግሊዝ እግር ኳስ አዲስ ክስተት ሆነው ከሚታዩ ተጨዋቾች አንዱ ሆኗል፡፡ ቢቢሲን ጨምሮ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ስለዚሁ ግብፃዊ ተጫዋች የሚያቀርቧቸው ትንታኔዎችና ሙገሳዎች በዓለም እየተስተጋባ ይገኛል፡፡

ግብፃዊው መሐመድ ሳላሕ በሊቨርፑል ክለብ የ11 ቁጥር መለያ ለብሶ ተስፋ በማይቆርጡት ሊቨርፑላውያን ዘንድ ድል አብሳሪ እስከመሆን ደርሷል፡፡ በግብፃውያን ዘንድም ‹‹የእኛ ሜሲ›› በሚል ቅጽል የሚቆለጳጵሰው ሳላሕ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በጋና (አክራ) በሚያከናውነው የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋቾች ምርጫ ከታጩት ውስጥ አንዱ ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል፡፡

በውድድር ዓመቱ በተሠለፈባቸው ግጥሚያዎች ሁሉ የተጋጣሚ ቡድኖችን ክልል በማሸበር እየታወቀ የመጣው መሐመድ ሳላሕ፣ ለዚህ ታላቅ ክብር መብቃት ችሏል፡፡ ለመጨረሻው ምርጫ ከበቁት አፍሪካውያን ኮከቦች ውስጥ የቡድን አጋሩ ሴኔጋላዊው ሲዲዮ ማኔ፣ ለጀርመኑ ቦርሽያ ዶርትሙንድ የሚጫወተው ኢሜሪክ ኡባ ሚያንግና ከሌሎችም ጋር ሲነፃፀር ቆይቷል፡፡ የ25 ዓመቱ መሐመድ ሳላሕ ቢቢሲና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች መገናኛ ብዙኃን የ2017 የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች አድርገው መርጠውታል፡፡

አዲሱ የፈረንጆች ዓመት እስኪጀመር 17 ኳሶችን በተቃራኒ ቡድን መረብ ላይ በማሳረፍ ከእንግሊዛዊ ሃሪ ኬን በአንድ የጎል ልዩነት ተበልጦ የኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን ደረጃም እንደያዘ ይገኛል፡፡

የእግር ኳስ ከዋክብት በሚፈተኑበት የእንግሊዝ ሊግ፣ በድንቅ ክህሎቱ እየተወደሰ የሚገኘው መሐመድ ሳላሕ፣ ከሊቨርፑል ስኬቱ በተጨማሪ ለሦስት አሥርታት ያህል ከዓለም ዋንጫ መድረክ ርቃ የቆየችው አገሩን ግብፅ በመጪው ክረምት ይከናወናል ተብሎ በሚጠበቀው ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ አብቅቷል፡፡

ግብፃዊው ባለ ግራ እግር ከአርጀንቲናዊ ባለ ግራ እግር ጥበበኛ እኩል ባይሆንም፣ የግብፃዊው ግራ እግርና ኳስ በተቃራኒ ግብ ክልል ውስጥ ሲገናኙ ግን ብዙ የሚያመሳስል ነገር እንዳለው ጭምር ምስክርነታቸውን የሚሰጡ አሉ፡፡ ይህንኑ መነሻ በማድረግ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ለግብፃውያን ብቻ ሳይሆን በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድም እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡

መሐመድ ሳላሕ ለግብፅ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ትልቁን ሚና ከተጫወቱት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹‹ፈርኦኖቹ›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን፣ ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ ሊበቃ የቻለው በእሱ ሁለት ጎሎች ብቻ ሳይሆን፣ ቡድኑ ለዚህ መድረክ ለመብቃት 28 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ሆኖበት ስለነበር ነው፡፡

ለሰሜናዊቷ ጥንታዊት አገር ታላላቅ ገድሎችን ከፈጸሙ ግብፃውያን መዝገብ እንዲካተት የሆነው መሐመድ ሳላሕ፣ በአገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታሕ አልሲሲ ጭምር ይህንኑ ክብር ማግኘቱ እየተነገረለት ይገኛል፡፡

ግብፃዊው የሊቨርፑል ኮከብ እንዲህ እንደ አሁኑ በእግር ኳሱ የገነነ ዕውቅናና ዝና ባይኖረውም፣ ለባዜል እግር ኳስ ክለብ ከ2012 እስከ 2014፣ ከዚያም ወደ እንግሊዝ አምርቶ ለቼልሲ ክለብ ከ2014 እስከ 2016 ተጫውቷል፡፡ ለግብፅ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 56 ጨዋታዎችን አድርጎ 36 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ የቻለ ተጨዋች መሆኑ ግለ ታሪኩ ያስረዳል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...