‹‹በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ በልዩ ልዩ የሥራ መስክ የተሰማራችሁ ወገኖችና የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ማኅበራዊ እሴቶችን ማለትም እውነት፣ ነጻነት፣ ፍትሕና ፍቅርን መርህ በማድረግ የሰላምና የመተባበር፣ ግጭትን በውይይት በመፍታት ረገድ በዓለም እንደቀድሞው የታወቅን ሕዝብ ሆነን እንድንቀጥል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ቤተ ክርስቲያናችን በእግዚአብሔር ስም ትማጠናለች፡፡››
ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት፣ የምሥራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት ሊቀመንበር፣ በአገሪቱ የተከሰተውን ወቅታዊ ‹‹ግጭት›› አስመልክቶ ነሐሴ 6 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. ካስተላለፉት የሰላም ጥሪ የተወሰደ፡፡ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሕዝብን ጥያቄ በየደረጃው አፋጣኝ መልስ በመስጠትና የሰላም ውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የማረጋጋትና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ጠንክረው እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አበክራ ትመክራለች ብለዋል፡፡