‹‹ስንፋታ እንደግስ››
‹‹እነዚህ ጉንዳኖች ፊት ለፊቴ ያሉ
የተጋጠን አጥንት ከበዋል በሙሉ
ካለሥጋ ቀርቶ ያ..አጥንት በዕርቃን
መሪ አጡ ከመሃል አንሂድ ባይ በቃን››
ይህ አንጓ ‹‹ዝክረ ጉንዳን!›› በሚል ርእስ መኳንንት መንግሥቱ የገጠመው ነው፡፡ ይህንና ሌሎች 80 ግጥሞቹን የያዘው የግጥም መድበል መሰንበቻውን ለኅጽመት አብቅቷል፡፡ ‹‹ስንፋታ እንደግስ›› የሚል ርእስ የሰጠውን መድበሉን ሐሙስ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በ11፡30 ሰዓት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል እንደሚስመርቅ ገጣሚው አስታውቋል፡፡ የመድበሉ ዋጋ 35 ብር ነው፡፡