Sunday, October 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ካፒታል ከ7.9 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ተዛማጅ ፅሁፎች

–  የብድር ክምችታቸው ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል

በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አቅማቸውን እያሳደጉ በመምጣት ከ7.9 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሳቸው ተገለጸ፡፡

ከኢትዮጵያ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ካፒታላቸውን በዚህን ያህል ደረጃ ማሳደግ የቻሉት በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት 33 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ናቸው፡፡

ይህም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የካፒታል መጠን 16ቱ የግል ባንኮች እስከ ሰኔ 2008 መጨረሻ ድረስ ከደረሱት አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታላቸው ጋር ሲነፃፀር ግማሽ ያህሉን ይሆናል፡፡ የግል ባንኮች አሁን የደረሱበት የተከፈለ ካፒታል 12.4 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

እንደ መረጃው ከሆነ ከ33 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ካፒታል ያላቸው አዲስ አበባ፣ ደደቢት አማራና ኦሞ የተባሉት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ይጠቀሳሉ፡፡

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እያሳደጉ ባሉት ካፒታል መጠን ልክም የተበዳሪዎችን ቁጥር በመጨመር ወደ 3.5 ሚሊዮን አድርሰዋል፡፡ ባለፉት አሥር ዓመታት ተከታታይ ዓመታዊ ሪፖርታቸው እንደሚያሳየው ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ዕድገት እየታየባቸው መሆኑ ነው፡፡

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ የሰጡት የብድር መጠንም ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ በ2006 በጀት ዓመት የብድር መጠኑ 2.04 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

በ2007 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ደግሞ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ የብድር ክምችት ከ20.2 ቢሊዮን ብር በላይ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ በየዓመቱ እያደጉ መምጣታቸውን ያመለክታል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ 26.8 ቢሊዮን ብር የነበረው ሀብታቸውም፣ በ2008 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከ31 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሳቸው ተጠቁማል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች