Wednesday, February 12, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የግል ኩባንያዎች ከግልጽ ጨረታ ውጪ አይስተናገዱም›› የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ...

‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የግል ኩባንያዎች ከግልጽ ጨረታ ውጪ አይስተናገዱም›› የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ቀን:

spot_img

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶችን ለአልሚዎች የሚያስተላልፈው በጨረታ ሒደት ብቻ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የግል ኩባንያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በጨረታ ሒደት ብቻ ተወዳድረው የሚያገኙት በውድድር የሚገኝ ጥቅም ማለትም ዝቅተኛ ዋጋ ለማግኘት፣ ግልጽነት ለማስፈን፣ የተሻሉ ቀዳሚ ኩባንያዎችን ለመሳብ፣ እንዲሁም ብዙ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ወደ ሥራ በማስገባት ረገድ ለሴክተሩም ሆነ ለአገር ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

ይሁንና በሪፖርተር የሐምሌ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ዕትም ‹‹ኩባንያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በድርድር ጭምር እንዲሳተፉ ተወሰነ›› በሚል ርዕስ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ በራሳቸው አቅም ወይም ከመንግሥት ጋር በሚደረግ ሽርክና በኃይል ማመንጨት ፕሮጀክቶች ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች፣ በጨረታ ብቻ እንዲስተናገዱ ያወጣውን ትዕዛዝ በማሻሻል ኩባንያዎቹ በድርድር ጭምር እንዲስተናገዱ መመርያ መሰጠቱን›› ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘገባ ወጥቶ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በላከው ማስተባበያ የወጣው ዜና መሠረተ ቢስ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የተጀመረውን ግልጽና አሳታፊ የግዢ ሒደት ጥርጣሬ ላይ የሚጥል ነው ብሏል፡፡ በመሆኑም በግል ባለሀብትም ሆነ በመንግሥት ፋይናንስ የሚመሩ ፕሮጀክቶች የግዥ ሒደት በተጀመረው የውድድር አካሄድ ብቻ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ይህ ዓይነቱ ዘገባ አገሪቱ በኢነርጂ ዘርፍ የምታካሂደውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሊጎዳ ይችላል ሲልም አሳስቧል፡፡

የጨረታ ሒደት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባና የተሻለ የግዥ ሒደት መሆኑን እንደ አቅጣጫ በማስቀመጥ የትግበራ ሒደቱ በሰፊው መጀመሩን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስገንዝቧል፡፡ በዚህ መሠረት በመተሐራ፣ በመቐለ፣ በሁመራ ጠቅላላው የ300 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን ማስገንባት የሚያስችል፣ እንዲሁም የጨሞጋ የዳ 280 ሜጋ ዋትና የታምስ 1,700 ሜጋ ዋት የውኃ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በግል ባለሀብቶች ለማልማት የሚያስችል ግልጽ የጨረታ ሒደት ተጀምሮ ብዙ ርቀት እንደተሄደበት ገልጿል፡፡

በተመሳሳይም በመንግሥት ባለቤትነት ደግሞ ከውኃ ኃይል ማመንጫዎች የገናሌ ዳዋ 6ኛ 254 ሜጋ ዋት፣ የዳቡስ 798 ሜጋ ዋት፣ የብርብር 407 ሜጋ ዋት፣ እንዲሁም የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በተመለከተ ደግሞ የደብረ ብርሃን 100 ሜጋ ዋት፣ የኢተያ 100 ሜጋ ዋት፣ የአይሻ 300 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጫዎችን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የጨረታ ሒደት ላይ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

‹‹በመሆኑም የተጀመረው የጨረታ ሒደት ውጤታማ እንደሚሆንና የተፈለገው ዝቅተኛ ዋጋ፣ ግልጽነትና ፍጥነት እንደሚኖረው በመንግሥትና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ እምነት በመኖሩ፣ በጨረታዎቹ እየተሳተፉ ካሉት አልሚዎችም ከፍተኛ ድጋፍና ተሳትፎ ያገኘ ነው፤›› በማለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የጋዛ ውዝግብ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የደቀነው ሥጋት

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማችና የቀድሞ የመካከለኛው ምሥራቅ የፖሊሲ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውክልና ለግሉ ዘርፍ ለማስተላለፍ ያቀዳቸው አገልግሎቶች

የከተማው አስተዳደር ካቢኔ ሰሞኑን ባሳለፈው ውሳኔ የተመረጡ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን...

የተገራ ስሜት!

እነሆ መንገድ ከስታዲዮም ወደ ጦር ኃይሎች። በጥበቃ የተገኘ ለበርካታ...