Friday, March 31, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የጃፓን ኩባንያ በአኩሪ አተር የሚዘጋጅ የውኃ ማጣሪያ ዱቄት አስተዋወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

–  ከቡና ገለባ በሚገኝ ኬሚካል ውኃ ለማጣራት አቅዷል

ፖሊ ግሉ ሶሻል ቢዝነስ የተባለው የጃፓን ኩባንያ፣ ከአኩሪ አተር ተጨምቆ የሚወጣ የውኃ ማጣሪያ ቅመም በመጠቀም የተበከሉ የውኃ አካላት ለመጠጥነት እንዲውሉ የሚያደርግ ጣቢያ ገነባ፡፡

ኩባንያው በቡራዩ ከተማ፣ ጠቼ አካባቢ የገነባው የሙከራ ማጣሪያ ለ50 ሺሕ ነዋሪዎች ንጹህ የመጠጥ ውኃ በቀላል ዘዴና በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አጣርቶ የሚያቀርብ ነው፡፡ ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. በቡራዩ ከተማ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ወቅት እንደታየው፣ ከአኩሪ አተር የሚዘጋጀው ማጣሪያ ዱቄት፣ ፖሊ ጉሌቲክ አሲድ ወይም ፖሊ ግሉ የሚል መጠሪያ ያለው ነው፡፡

ይህ ማጣሪያ ዱቄት፣ በአንድ ሚሊ ሌትር እስከ አንድ ሺሕ ሌትር ውኃ በ15 ደቂቃ ውስጥ አጣርቶ ለመጠጥነት ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ሊቀመንበርና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ካኔቶሺ ኦዳ አስረድተዋል፡፡ በአንድ ጊዜ 150 ሜትሪክ ቶን ውኃ ከወራጅ የወንዝ ውኃ የሚያጣራው ጣቢያ፣ የደፈረሰውን ቆሻሻ ውኃ በመጀመሪያው ምዕራፍ ዱቄቱ ሲገባበትና ሲማሰል፣ ድፍርሱን ነገር ሁሉ በአንድ እያሰባሰበ አጣብቆ የሚያዘቅጥ ነው፡፡

በመቀጠልም በሁለተኛው የማጣራት ዑደት፣ የተጣራው ውኃ ፊልተር እንዲሆንና ይበልጥ ከበካይ ንጥረ ነገሮቹ እንዲጸዳ የሚደረግበት ሒደት ሲሆን፣ የመጨረሻው ምዕራፍ ግን ባክቴሪያና ሌሎች ጎጂ ተህዋስያንን ለመግደል ክሎሪን ታክሎበትና ታክሞ ለመጠጥነት የሚውልበት ነው፡፡ 

ይህ ሒደት በቀላሉ የሚተገበር ሲሆን፣ ምንም ዓይነት የተለየ የሙያ ክህሎት የማይጠይቅና ማንም ሰው ሊተገብረው እንደሚችል ዶ/ር ኦዳ ይናገራሉ፡፡ ለአንድ ሚሊ ሌትር ፖሊ ግሉ አንድ ዶላር የሚጠይቁት ዶ/ር ኦዳ፣ የትራንስፖርትና መሰል ወጪዎች ታክለውበት አንድ ሚሊ ሌትሩ በሁለት ዶላር እንደሚቀርብ ገልጸዋል፡፡

በመላ አገሪቱ ይህንን የውኃ ማጣሪያ ማስፋፋት እንደሚፈልጉና በአምስት ዓመት ውስጥም በአገሪቱ ያለውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፉ ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከፖሊ ግሉ ባሻገር ሌላ የውኃ መጣሪያ አማራጭ ሊኖር እንደሚችል ጠቅሰው፣ በተለይ በቡና ላይ ባደረጉት ምልከታ ለውኃ መጣሪያነት የሚውል ኬሚካል በቡና ገለፈት ውስጥ መኖሩን እንደተገነዘቡ ጠቅሰዋል፡፡

ይህንንም መነሻ በማድረግ ከቡና ገለፈት ማጣሪያ ለማበልጸግ እንዲቻል የሚመለከታቸው የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች አብረዋቸው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ወደፊትም የፖሊ ግሉ ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ በአገር ውስጥ የማቋቋም ሐሳብ እንዳላቸው ዶ/ር ኦዳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ከአሥራ አስምት ዓመት በፊት የኪዮ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ውጤትን መነሻ በማድረግ ያበለፀጉት የአኩሪ አተር መጣሪያ፣ ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ ገበያ ላይ ውሎ በባንግላዴሽ፣ በታንዛንያ፣ በሶማሊያ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ መተግበር ጀምሯል፡፡

በቡራዩ ከተማ የተገነባውን የውኃ ማጣሪያ ጣቢያ የጃፓን ኤምባሲ በአንድ መቶ ሺሕ ዶላር ወጪ እንዳስገነባው ታውቋል፡፡ የጃፓን መንግሥት እ.ኤ.አ. ከ1989 ጀምሮ በአነስተኛ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ራስ አገዝ በሆኑ አገር በቀል ተቋማት አማካይነት የሚካሄዱ ልዩ ልዩ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የሚያቃልሉ አነስተኛ ፕሮጀክቶችን በገንዘብና በቴክኒክ ሲደግፍ ቆይቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች