Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ይድረስ ለሪፖርተርየጎዳና ነጋዴዎችን ለአደጋ ከሚዳርግ ማሳደድ ታቀቡ

የጎዳና ነጋዴዎችን ለአደጋ ከሚዳርግ ማሳደድ ታቀቡ

ቀን:

በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ደንብ እንዲያስከብሩ ቅጠልያ ለብሰው የሚዞሩ ደንብ አስከባሪዎችን ከተዋወቅን ብዙ የሚባሉ ዓመታት አስቆረናል፡፡ ነገር ግን መለስ ብለን እነዚህ ደንብ አስከባሪዎች ወይም ደንብ እየተባሉ በአጭሩ የሚጠሩት ሥርዓት አስከባሪዎች ሥርዓት የማያውቁ፣  ሥርዓትና ደንብ ጥሰው የሥርዓት ጠበቃ ለመሆን የሚዳዳቸው ናቸው፡፡

ሁሉንም ለመውቀስ ባይዳዳኝም በየጎዳናው የማያቸው ነውጥ ፈጣሪዎች ግን እነዚሁ ደንብ አስከባሪ ተብዬዎቹ በርካታ ቅጠል ለባሾች ናቸው፡፡ በመሠረቱ ሥርዓት አልበኛነታቸው የሚጀምረው ከአለባበሳቸው፣ ከንጽህናቸው፣ ከአነጋገራቸውና ከጠቅላላው ውሏቸው ይመስላል፡፡

የጎዳና ንግድ ተገቢ ነው እያልኩ አይደለም፡፡ የጎዳና ንግድ መበረታታት አለበት እያልኩም አይደለም፡፡ እርግጥ የጎዳና ላይ ንግድ በሌላው ዓለም የቱሪስት መስህብ መሆኑንም መጥቀስ ይገባል፡፡ እንደ ኢስታንቡል ባሉ ከተሞች በቆሎ ሻጮች ባማረ ተንቀሳቃሽ ጋሪ ላይ ደርድረው የሚሸጡት በቆሎ፣ በፖሊስ አባራሪ ወይም በእኛው ደንብ ለባሾች ወከባ የለበትም፡፡

- Advertisement -

እርግጥ ነው ወደ ዋና የገበያ ቦታዎች ሲኬድ እንደኛ ያለው የመንገድ ላይ ግርግር ሥርዓት ስቶ አይታይባቸውም፡፡ ነገር ግን የጎዳና ንግድ ለነጋዴዎቹ የዕለት ጉርስ ማግኛ ከመሆን አልፈው፣ ለመንግሥትም የግብር ምንጭ እንደሆኑ እዚሁ እኛው አገር እያየን ነው፡፡ በየሣምንቱ በሚከለሉት የጎዳና መነገጃ  ቦታዎች መንግሥት ከእያንዳንዱ ነጋዴ ቀረጥ እንደሚሰበስብ ለማወቅ ስድስት ኪሎ ያሬድ ትምህርት ቤት አካባቢ በሰንበት ጎራ ማለት በቂ ነው፡፡

እንዲህ ያሉ ለሰዎች ጠቃሚነት ያላቸውን አሠራሮች በማዛመት ፈንታ እንደ ፊጋ በሬ ሕዝብ እያስደነበሩ፣ እያዋከቡና እያንገላቱ ሽብር መፍጠር ግን ከደንብ አስከባሪ የሚጠበቅ ሥርዓት አይሆንም፡፡

በሜክሲኮ አደባባይ የሚታው ግን ይህ ነው፡፡ ከየአቅጣጫው በሜክሲኮ አደባባይ አድርጎ እንደየፊናው የሚመላለሰው የሕዝብ ቁጥር ሠርክ ልጓም የለውም፡፡ በተለይ ከሥራ መውጫና መግቢያ ሰዓት ላይ የሚታው የሰው ትርምስ አጀብ የሚያሰኝ ነው፡፡ በዚህ የሰው ውቅያኖስ ውስጥ የደራ ገበያ ማቆም ያማራቸው ወጣቶች በላስቲክ ያንጠለጠሉትን ሸቀጥ አንጥፈው በእግረኛው እግር ሥር እየገቡ መሸቀጣቸው አግባብ አይደለም፡፡ ይህ አግባብ ያልሆነ ተግባር ግን አግባብ ባልሆነ አካሄድ አይደለም ምላሽ ሊሰጠው የሚገባው፡፡

በመንግሥት ተዋቅሮና እንደ አቅሙም ሥልጣን ተሰጥቶት የሚሠራ ተቋምን ወክለው የሚሠሩ ባልደረቦቹ እንዳሻቸው ሰው እንደ እንስሳ እያንፈራጠጡ፣ እየደበደቡና እያዋከቡ ወዳሻቸው ቦታ የመውሰድ መብት የትኛው ሕግ እንደሰጣቸው ይገለጽልን፡፡ የትኛውም መብት ይሆን ራሱ ዳኛ፣ ራሱ ከሳሽ እንዲሆኑ ያጫቸው? ኑሮ አቀበት በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ተገቢውን ሥርዓት ጠብቆና አውቆ ጥፋተኛውን እንደጥፋቱ ማስተናገድ ሲገባ፣ እየቶሽሎኮለኩ የሌባና የፖሊስ ፍጥጫ ውስጥ መግባት፣ እግረኛውን ማወክና ለጠብ እንዲጋበዝ የሚገፋፋ አካሄድ መከተል ሊታረም የሚገባው ነው፡፡

በተለይ በመጡበኝ፣ በደረሰቡኝ ሥጋት እግሬ አውጪኝ የሚፈረጥጡ የመንገድ ላይ ነጋዴዎች ለመኪና አደጋ ሲዳረጉ ማየትም ቀላል ነገር  ነው፡፡ ጥርስ እየተሳበሩ የሚጓተቱትንም በብዛት እንድንመለከት ተገደናል፡፡ በአንጻሩ መንገድ ላይ ሽንቱን የሚያርከፈክፈውን፣ እንደየመጠኑ ከአንድ የውኃ ፕላስቲክ ጀምሮ፣ የማስቲካ ልጣጭና የመሳሰለውን ነገር ሁሉ በየመንገዱ እያዘራ የሚሄደውንስ የማትቆጣጠሩ ደንበኞች እንደው ምን ያላችሁት ናችሁ?

የከተማውን መሥሪያ ቤቶች አጥሮች በአስቀያሚ ማስታወቂያ የሚያዥጎደጉዱትን ምነው አትነኳቸውሳ? ምነዋ የእግረኛ አልበቃ ብሏቸው፣ የመኪና መንገድ እያጠሩ ሕንጻ የሚሠሩትን፣ የግንባታ ዕቃ አራግፈው ማን አለብኝ የሚሉትን፣ የትራፊክ ፍሰት የሚያስታጉሉትን ምነዋ አታዩ፡፡ ዕድሜ ልክ ድሃ የመንገድ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ያጠነጠነ የሚመስለው አደን፣ የሆነ የሚጠቀሙበት ነገር ቢኖር እንጂ፣ የሚሸጧቸውን ቁሳቁሶች ለመቀማት እንጂ እውነት የሕግ መከበር፣ የደንብና የሥርዓት መስፈን አገብግቧቸው ቦክስ ሲሰናዘሩ ይውላሉ ብሊ አፍን ሞልቶ መናገር ለማንም የከተማው ነዋሪ የሚቻለው አይደለም፡፡

ስለዚህም ደንብ እናስከብራለን እያሉ ደንብ የሚበጠብጡትን መንግሥት ያውቃቸው እንደሆነ አደብ ቢያስገዛቸው፣ አለያ የማውቃቸው፣ ቅጥራቸው በየሱቁ ለሚወረውርላቸው ነጋዴ ከሆነም ሚናቸው ይለይና አደብ የሚገዙበት መንገድ ይፈለግ፡፡ ለጎዳና ነጋዴዎችም የይስሙላ ያይደለ፣ ነግደው አትርፈው የሚገቡበት ትክክለኛ የንግድ ቦታ ይከለልላቸውና በዚያ መሠረት እንዲሠሩ ይደረግ፡፡ ሞቅ ሲለው እየቀማ፣ ሲመስለው ደግሞ ኑ በዚህ ጎዳና ነግዱ የሚል የመንግሥት አካልም ይታረም፡፡ ወጣቶቹ ለዘለቄታቸው የሚያዋጣ መፍትሄ ይሻሉና ሁሉም ይመልከታቸው፡፡

(አይናለም ይረጋ፣ ከመናኸሪያ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...