‹‹በአንድ በኩል ስታስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ እኔ የትግራይ ሰው ነኝ፣ እኔ አማራ ነኝ ብሎ አፍ ሞልቶ መናገሩም አለማወቅ ይመስለኛል፡፡ በሴት አያቶቻችን በራፍ ላይ ማን እንዳለፈ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? የኔን ጥሩ ኦሮሞነት እግዚአብሔርና የሴት አያቶቼ ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ የሁሉንም እንዲሁ፡፡››
ገጣሚና ጸሐፊ ሰሎሞን ደሬሳ፣ ከዓመታት በፊት ሪፖርተር መጽሔት ስለ ኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ላነሳለት ጥያቄ ከሰጠው መልሰ የተቀነጨበ፡፡ ጦር ባለፈ ቁጥር በመዋለድ፣ በንግድ በመገናኘት፣ ተቸግሮ ከአገር ወጥቶ ሌላ ቦታ በመኖር [ሰዉ] ይቀላቀላል ሲልም ተናግሮ ነበር፡፡