አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 1 ኪሎ ከግማሽ የተከተፈ የበግ ሥጋ
- በቁመቱ የከተፈ ቀይ ሽንኩርት (ሦስት ጭልፋ)
- 1 ኪሎ ግራም በስሱ የተቆረጠ ድንች
- 1 ሊትር የአትክልት መረቅ
- 4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ፐርስሊ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቂቤ
አዘገጃጀት
- ሥጋውን በጨውና በቁንዶ በርበሬ መለወስ
- ድንቹንና ሽንኩርቱን ለብቻው መቀላቀል
- የተለወሰውን ሥጋ በተዘጋጀው ድስት ውስጥ ከስር አድርጎ የድንቹንና የሽንኩርቱን ቅልቅል ከላይ መጨመር
- መረቁን መጨመር (መረቁ ድንቹን መሸፈን የለበትም)
- ከላዩ ዘይት መጨመር
- ፉርኖ ቤቱን አሙቆ ድስቱን በመክተት እንዲበስል መተው
- ድንቹ ከሥጋው ጋር እንዲጣበቅ በጭልፋ መጫን፣ እንዲበስልም ማድረግ
- ሲበስል ድንቹ ላይ የቀለጠውን ቅቤ አፍስሶ የደቀቀ ፐርስሊ ነስንሶ ማቅረብ
- ደብረወርቅ አባተ ሱ ሼፍ፣ ‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (1993 ዓ.ም.)