Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፍርድ ቤት በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ላይ የቀረቡ ምስክሮችን መስማት አያስፈልግም...

ፍርድ ቤት በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ላይ የቀረቡ ምስክሮችን መስማት አያስፈልግም አለ

ቀን:

ተጠርጣሪው ለዘጠኝ ቀናት የረሃብ አድማ ማድረጉን አስታወቀ

በግላቸው የፌስቡክ አድራሻ በተለይ ከአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተነስቶ የነበረው አመፅ እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ቀስቃሽ መጣጥፎችንና ሌሎች መረጃዎችን በማስተላለፍ ተጠርጥሮ የሽብር ወንጀል ክስ በቀረበበት፣ የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ላይ ዓቃቤ ሕግ የቆጠራቸውን የደረጃ ምስክሮች መስማት እንደማያስፈልግ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የተጠርጣሪውን የአቶ ዮናታን ተስፋዬን ክስ እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ እንዳስታወቀው፣ ዓቃቤ ሕግ የቆጠራቸው የደረጃ ምስክሮች (ተጠርጣሪው በራሱ ፈቃድ ፓስወርድ ሰጥቶ በፌስቡክ አድራሻው የጻፋቸውን መጣጥፎች ታትመው ሲወጡና የራሱ ጽሑፎች መሆናቸውን በፊርማው ሲያረጋግጥ በምስክርነት ፖሊስ ጣቢያ የተገኙ) ሊመሰክሩ የማይችሉት፣ ተጠርጣሪው የራሱ መሆኑን አምኖና በፊርማው አረጋግጦ በቀረቡት ማስረጃዎች ላይ መሆኑን ጠቁሞ፣ የፍርድ ቤቱን ጊዜ ከማጥፋት ባለፈ የሚጨምሩትም ሆነ የሚቀንሱት ነገር እንደሌለ በመንገር ምስክሮቹ መሰማታቸው እንደማያስፈልግ ገልጿል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የደረጃ ምስክሮቹ የሚመሰክሩበትን ጭብጥ ሲያሲዝ፣ ፍርድ ቤቱ ከላይ የገለጸውን በመናገሩና የተጠርጣሪው ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ ደንበኛቸው ያልካደው፣ አምኖና ፈርሞ ባረጋገጠበት ሁኔታ የፍርድ ቤቱን ጊዜ ማጥፋት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ መቃወሚያ በማቅረባቸው ነው፡፡

ዓቃቤ ሕጉ የደረጃ ምስክሮቹ መሰማት አለባቸው በማለት የተከራከረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪው እንዳልካደና መስማት እንደማያስፈልግ ቢገልጽም፣ ዓቃቤ ሕጉ ግን ክርክሩ ጉዳዩን እያየው ባለው ፍርድ ቤት ብቻ እንደማያበቃ በመግለጽ ሊከራከር ቢሞክርም፣ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን በማጠንከር ምስክሮቹን አልፏቸዋል፡፡

ሌላው ተከሳሽ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ማረሚያ ቤቱ ግን እንደተፈረደበት ታራሚ በጨለማ ቤት ውስጥ እንዳሠረው በመግለጽ ያቀረበውን አቤቱታ በሚመለከት፣ ማረሚያ ቤቱ ‹‹ስሜን እያጠፉ ነው›› የሚል ምላሽ መስጠቱን ገልጿል፡፡

አቶ ዮናታንም አቤቱታ ካቀረበ በኋላ በር እንደተከፈተለትና ቴሌቪዥንም እንደገባለት በመናገር ችግሩ መፈታቱን አስረድቷል፡፡ ነገር ግን ከቤተሰብ ማለትም ጠያቂዎቹን በሚመለከት ከፍተኛ ችግር ላይ መሆኑን አመልክቷል፡፡ የእሱ ቤተሰቦች ከሌሎች ታራሚና ታሳሪዎች ቤተሰቦች የመጠየቂያ ሰዓት ውጪ ለአጭር ሰዓት እንዲያገኙት በመደረጋቸው፣ ቤተሰቦቹ በአግባቡ እየጠየቁት እንዳልሆነና ሊያገኙት እንዳልቻሉም አስረድቷል፡፡ በዚህ ችግር ለዘጠኝ ቀናት ያለ ምግብ (የረሃብ አድማ) መቆየቱን ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤት የሚደርስበትን ችግር በአስተዳደር በኩል የሚፈታ እንደሆነ እየገለጸ ስለሚያልፍ ከፍተኛ በደል እየደረሰበት መሆኑን አስረድቶ፣ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ የላከው ፍርድ ቤቱ ስለሆነ በአስተዳደር በኩል የሚለውን ትቶ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በአስተዳደር በኩል የሚለው አሠራር መሆኑን ገልጾ፣ በጽሑፍ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ኃላፊውን በማስጠራት ጥብቅ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፍና ቅጣትም እንደሚጥል አስታውቋል፡፡ አቶ ዮናታን የተናገረውን በጽሑፍ እንዲያቀርብ በማዘዝ በመዝገቡ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...