‹‹ንባብ ለሕይወት›› በሚል ከሐምሌ 14 እስከ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ላይ አዳም ረታ የወርቅ ብዕር ተሸልሟል፡፡ አዳም ጭጋግና ጠል፣ ማህሌት ግራጫ ቃጭሎች፣ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ፣ ሕማማትና በገና፣ አለንጋና ምስር፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ በተሰኙ የአጫጭር ልቦለድ ስብስቦች መጻሕፍቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ አምና መረቅ ዘንድሮ ደግሞ የስንብት ቀለማት የተሰኙ መጻፍትን አሳትሟል፡፡ የዐውደ ርዕዩ አዘጋጆች በየዓመቱ በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ደራሲያንን የሚሸልሙ ሲሆን፣ አምና አምባሳደር ዘውዴ ረታ ሽልማቱን ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡