Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊከዛምቢያው አደጋ የተረፉ 25 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

  ከዛምቢያው አደጋ የተረፉ 25 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

  ቀን:

  ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ላይ የነበሩና ዛምቢያ ውስጥ በከባድ ተሽከርካሪ ኮንቴይነር ውስጥ ተጭነው የመታፈን አደጋ ከደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን መካከል፣ 25ቱ በሰላም ወደ አገራቸው እንዲገቡ ማድረጉን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ፡፡

  ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. 19 ኢትዮጵያውያን በተጫኑበት ተሽከርካሪ ኮንቴይነር ታፍነው ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል፡፡ አስከሬናቸውም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙ አይዘነጋም፡፡ ወደ አገራቸው የተመለሱትን 25 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጨምሮ 76 ሰዎች ከአደጋው ተርፈዋል፡፡

  ሁሉም ተመላሾች ወንዶች እንደሆኑና ዕድሜያቸውም በ18 እና በ30 መካከል እንደሆነ የአይኦኤም መግለጫ አመልክቷል፡፡ መግለጫው በተጨማሪም አደጋው የደረሰው ስደተኞቹ እስከ ዘጠኝ ወራት ሊወስድ በሚችል ጊዜ የኬንያ፣ የታንዛኒያና የዛምቢያ ድንበሮችን በተሽከርካሪ በማቋረጥ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ ጥረት እያደረጉ እያለ እንደሆነ ገልጿል፡፡

  አይኦኤም ለተመላሾቹ ወደ ትውልድ ቀያቸው መመለሻ ዕርዳታ ማድረጉንም ገልጿል፡፡ ተመላሾቹ ለሕገወጥ አዘዋዋሪዎች እስከ 90,000 ብር ድረስ መክፈላቸውንም መግለጫው ጠቁሟል፡፡ አይኦኤም እ.ኤ.አ. በ2016 ብቻ 79 ስደተኞች ከዛምቢያ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ድጋፍ ማድረጉን አመልክቷል፡፡

  በኢትዮጵያ የአይኦኤም ልዑክ መሪ ማውሪን አቺየንግ ‹‹በርካታ ስደተኞች ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችን መምረጣቸው በሕገወጥ ስደት ዙሪያ ኅብረተሰቡን በተለይም ሩቅ ቦታ ያሉትን የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ እንዳለብን ያሳያል፤›› ብለዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...