አስፈላጊ ግብዓቶች
- 1 ዶሮ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 2 ቲማቲም
- 4 በስሱ የተቆረጠ ቤከን የዓሳማ ሥጋ
- ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ስኳር፣ ዳቦ የተጠበሰ
አሠራር
- ዶሮውን አጥቦ ሆድ ዕቃውን ማውጣት፣
- ትንሽ ውኃ አፍልቶ ዶሮውን በመጠኑ መቀቀል፡፡
- የዶሮውን ብልት አውጥቶ በጥንቃቄ ሥጋውን ከአጥንቱ መለየት፡፡
- ፍም ላይ ወፍራም የብረት ወንፊት አስቀምጦ ሥጋውን እላዩ ላይ አድርጎ እያገላበጡ መጥበስ፡፡
- ቲማቲሙን ሁለት ቦታ ቆርጦ ከጨው፣ ከቁንዶ በርበሬና ከስኳር ጋር ማደባለቅ፡፡
- ፍሙ ላይ ባለው ወፍራም የብረት ወንፊት የቲማቲሙን ድብልቅ እያገላበጡ መጥበስ፡፡
- ቤከኑን በመጥበሻ መጥበስ፡፡
- የተዘጋጀውን ዶሮ፣ ቲማቲምና ቤከን ከተጠበሰ ዳቦ ጋር ማቅረብ፡፡
ሁለት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)