አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 1 ሙሉ የበግ ወይም የፍየል አንጐል
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 2 የሾርባ ማንኪያ ፍሬው ወጥቶ የደቀቀ ቃርያ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 1 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
- 1 የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን፣ ቃርያውንና ነጭ ሽንኩርቱን ደባልቆ በቅቤ ማቁላላት፤
- ሚጥሚጣና ነጭ ቅመም ጨምሮ ለትንሽ ጊዜ ማማሰል፤
- የተዘጋጀውን አንጐል መጨመርና እንዳያር ተጠንቅቆ ለብለብ ማድረግ፤
- ጨውን አስተካክሎ በትኩሱ ለገበታ ማቅረብ፤
ደብረወርቅ አባተ ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)