Monday, October 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትሴሲሊያን

  ሴሲሊያን

  ቀን:

  ሴሲሊያን (caecilian) እግር የለሽ፣ ሸንቃጣ የመሬት ትል የመሰሉና አካላቸው በቅርፍ የተሸፈኑ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጣም አጭር ወይም ጭርሱኑም ምንም ጅራት የሌላቸው ናቸው፡፡ ጎሬ ውስጥ ነዋሪ እንደመሆናቸው ምግባቸውም ትላትሎችና ሌሎች አነስተኛ እንስሳት ናቸው፡፡ ለእንዲህ ዓይነት የጎሬ የዳበረ ዕይታ ስለማያስፈልግ አብዛኞቹ አይነስውሮች ናቸው፡፡ ነገር ግን የዳበረ የመዳሰስ ችሎታ አላቸው፡፡

  ርባታቸው ከሌሎቹ እንቁራሪት አስተኔዎች የተለየ ነው፡፡ ውስጣዊ ፅንሰት ያካሂዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ዕንቁላል ጣዮች ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደ አጥቢዎች ፀንሰው የሚወልዱ ናቸው፡፡ ፅንሱም የሚያድገው ከእናትየዋ ማሕፀን በሚያገኘው ምግብ ነው፡፡ በሕይወትም ከአምስት እስከ ሃያ ዓመት ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

  • ማን ይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img