Tuesday, May 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የተወሰነው በውጭ ተፅዕኖ እንዳልሆነ ተገለጸ

የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የተወሰነው በውጭ ተፅዕኖ እንዳልሆነ ተገለጸ

ቀን:

ኢሕአዴግ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የወሰነው፣ በውጭ ተቋማትና መንግሥታት ተፅዕኖ እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ኢሕአዴግ የወሰዳቸው ዕርምጃዎች በተፅዕኖ የመጡ አይደሉም፡፡

‹‹የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው የበለጠ ጥልቀት እንዲኖረው እየተደረገ ያለው ዕምርጃ ለአገሪቱ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ትልቅ ፋይዳ አለው፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

የውጭ ግንኙነትና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂው ከውስጥ ወደ ውጭ እንደሚመለከትና በአገር ውስጥ ሰላም እንዲመጣ፣ ዴሞክራሲ ሥር እንዲሰድ፣ መልካም አስተዳደር እንዲጎለብት የሚወሰድ ዕርምጃ ሁሉ ለውጭ ግንኙነት ስኬት አስፈላጊ መሆኑን አቶ መለስ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለፉት ሦስትና አራት ወራት በተለይም አገሪቱ ቀውስ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ከውጭ ግንኙነቱ አኳያ ምን ዓይነት አሉታዊ ተፅዕኖዎች ነበሩ? የሚል ጥያቄ ከሪፖርተር ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ፣ በመንግሥት በኩል የተወሰዱ ዕርምጃዎች በተፅዕኖ የመጡ እንዳልሆኑና አገሪቱ ከሌሎች አገሮች ጋር ባላት ግንኙነት ላይም የተለየ ተፅዕኖ እንደሌለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የበለጠ እንዲጠናከርና የፖለቲካ ምኅዳሩ እንዲሰፋ የእኛ ወዳጆች ፍላጎት አላቸው፡፡ ይህ ጤነኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የሚወሰዱ ዕርምጃዎች ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ተብለው የሚወሰዱ ናቸው እንጂ፣ የየትኛውንም አገር ፍላጎት ለማሟላት ተብለው የሚወሰዱ አይደሉም፤›› ብለዋል፡፡

አቶ መለስ ይህን ቢሉም፣ በአገሪቱ ውስጥ ያለው ቀውስ በአስቸኳይ እንዲቆምና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ዓለም አቀፍ ተቋማትና የተለያዩ አገሮች ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ለዚህም ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ብድርና ድጋፍ እንዲቆም ሲወተውቱ ነበር፡፡  

በሌላ ዜና በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት ወደ አውሮፓና ሌሎች አገሮች ለመሻገር ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ሊቢያ ውስጥ በችግር ላይ መሆናቸው በተደጋጋሚ ጊዜ ሲነገር ቢሰማም፣ እስካሁን ድረስ ከችግሩ ነፃ ሆነው ወደ አገራቸው መመለስ እንዳልቻሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ለባርነት ሲሸጡና ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ከተለቀቁ በኋላ፣ መንግሥታት ዜጎቻቸውን ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ ከአፍሪካ አገሮች ቀዳሚ በመሆን ችግር ላይ ያሉ ዜጎቿን ያስወጣችው ናይጄሪያ ስትሆን፣ ሌሎች አገሮችም በእንቅስቃሴ ላይ ስለመሆናቸው ሲናገሩ ተደምጧል፡፡

በሊቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን መናገር ከጀመረ ከአንድ ወር በላይ ቢያስቆጥርም፣ ወደ አገር ቤት የተመለሱ እንደሌሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ መለስ እንደተናገሩት፣ ካይሮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካይነት ከ30 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የጉዞ ሰነድ ተሰጥቷል፡፡ የጉዞ ሰነድ የተሰጣቸው ዜጎች መቼ ወደ አገር ቤት እንደሚመለሱ ግን አልታወቀም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...