Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሠራተኞች አድማ ሥራ አቆመ

ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሠራተኞች አድማ ሥራ አቆመ

ቀን:

ደርባ ሚድሮክ ከታኅሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሠራተኞች አድማ ምክንያት ሥራ አቆመ፡፡ አድማው ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባበት ዕለት ድረስ የቀጠለ ሲሆን፣ የደርባ ሚድሮክ ማኔጅመንትም ሆነ የኦሮሚያ ክልል አድማውን ማስቆም አለመቻላቸው ታውቋል፡፡

የደርባ ሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ስድስት ያህል ዓላማቸው ግልጽ ያልሆነ ሠራተኞች ለሌሎች ሠራተኞች ማስፈራርያ በመላክ ሥራ እንዲቆም አድርገዋል፡፡

‹‹የሲሚንቶ ምርት ቆሟል፡፡ በአጠቃላይ ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቁሟል፡፡ በክምችት ያለውንም ምርት ለገበያ ማቅረብ አልተቻለም፤›› ሲሉ አቶ ኃይሌ ገልጸው፣ ‹‹ችግሩን ከወረዳውም ሆነ ከዞኑ ጋር በመነጋገር ለመፍታት ቢሞከርም ሊሳካ ግን አልተቻለም፤›› ሲሉ ደርባ ሚድሮክ የገጠመውን ችግር አስረድተዋል፡፡

የሥራ ማቆም አድማ ከመመታቱ በፊት የግዙፉ ደርባ ሚድሮክ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጠይቀው ነበር፡፡ በተለይ መንግሥት ብር ከዶላር ጋር ያለውን ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በማድረጉ፣ ሠራተኞች 15 በመቶ ደመወዝ እንዲጨመርላቸው መጠየቃቸውን አቶ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማኔጅመንት ከሠራተኛ ማኅበሩ ጋር ከመከረ በኋላ ስምምነት ላይ በመድረሱ፣ 25 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

‹‹ደርባ ሚድሮክ በሠራተኞች ከተጠየቀው 15 በመቶ ጭማሪ አሥር በመቶ ያህል በመጨመር 25 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል፤›› ሲሉ አቶ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡   

ይህ ጥያቄ ከተፈታ በኋላ ደግሞ የመዋቅር ለውጥ እንዲደረግ ከሠራተኞች ጥያቄ መቅረቡን ጠቁመዋል፡፡ ይህን የመዋቅር ጥያቄ ለማየት የሦስት ወራት ጊዜ እንዲሰጥና ኮንሰልታንት ተቀጥሮ እንዲሠራ ብንስማማም፣ ዓላማቸው ግልጽ ያልሆኑ ሠራተኞች በተለያዩ ክፍሎች ለሚሠሩ ሠራተኛው ማስፈራርያ በመላክ የሥራ ማቆም አድማ እንዲመታ አድርገዋል፤›› ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የደርባ ሚድሮክ ሠራተኞች ማኅበርም ተሰሚነት እንዳጣ አቶ ኃይሌ አስታውቀዋል፡፡

ችግሩን የኦሮሚያ ክልል መዋቅሮች በተለይም ወረዳውና ዞኑ ሊፈቱት ባለመቻሉ፣ ‹‹በዚህ ሳምንት ጉዳዩን ወደ ፌዴራል መንግሥት እንወስደዋለን፤›› ሲሉ አቶ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡

ደርባ ሚድሮክ 740 ቋሚ ሠራተኞችና 460 ጊዜያዊ ሠራተኞች አሉት፡፡ በአሁኑ ወቅት ደርባ ሲሚንቶ ወደ ገበያ እየቀረበ አለመሆኑ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...