ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት በሚመሩት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ሦስተኛ መደበኛ ጉባኤ ወቅት የተናገሩት ኃይለ ቃል፡፡ በኢትዮጵያ እያከተመላቸው ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች መካከል የአዋሽ፣ የነጭ ሳር እንዲሁም የባቢሌ ብሔራዊ ፓርኮች ህልውና ወደ መጥፋቱ መቃረቡን በማስመልከት የክልል አመራሮች የታሪክ ተጠያቂዎችም ጭምር እንደሚሆኑ በማስጠንቀቅ ባደረጉት ንግግር ጆሮ ያላቸው እንዲሰሙ፣ ሕዝቡም የምክር ቤቱም አባላት ጫና እንዲያሳድሩባቸው አስረግጠው አሳስበዋል፡፡