Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለሕመምተኛው አቶ ሀብታሙ አያሌው ሦስት ሐኪሞች የፈረሙበት የሕክምና ሪፖርት ለፍርድ ቤት ቀረበ

ለሕመምተኛው አቶ ሀብታሙ አያሌው ሦስት ሐኪሞች የፈረሙበት የሕክምና ሪፖርት ለፍርድ ቤት ቀረበ

ቀን:

ከፍተኛ የኪንታሮት ሕመም ምክንያት በማደንዘዣ ለሚገኘው የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) አመራር ለነበረው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ሦስት ሐኪሞች የፈረሙበት የሕክምና ሪፖርት (ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ቤተሰቦቹ ገለጹ፡፡ ሕመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ አገር ውስጥ ባሉ የሕክምና ተቋማት መታከም ስለማይችል፣ ወደ ውጭ አገር ሄዶ መታከም እንዳለበት ክትትል የሚያደርግበት ካዲስኮ አጠቃላይ ሆስፒታል በመወሰኑ፣ ሁለት ሐኪሞች በሕክምና ሪፖርቱ ላይ ፈርመው አንድ ሐኪም ሲጠበቁ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ሦስተኛው ሐኪምና የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ለዕረፍት ከሄዱበት አሜሪካ በመመለሳቸውና በመፈረማቸው፣ ማክሰኞ ሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም ለጊዜው ዳኞች ባለመሟላታቸው እስከ ከሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚሰጥና በጽሕፈት ቤት ወይም በመዝገብ ቤት እንዲከታተሉ፣ በቅርቡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ዳኜ መላኩ ነግረዋቸው መመለሳቸውን ቤተሰቦቹ ገልጸዋል፡፡ አቶ ሀብታሙ ሕክምናውን በቅርቡ ካላገኘ ሕመሙ ወደ ካንሰር ሊቀየር እንደሚችል፣ ከዚያ በኋላ ሊድን እንደማይችል ሐኪሞቹ ማስጠንቀቃቸውንም ቤተሰቦቹ አክለዋል፡፡ አቶ ሀብታሙ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ብሎበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት በክርክር ላይ ሲሆን፣ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ከአገር እንዳይወጣ መታገዱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ