Sunday, April 14, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በደሌ ቢራ የተጣራ ውኃ ለመልቀቅ የ24 ሚሊዮን ብር ማሽን ተከለ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በደሌ ቢራ ፋብሪካ በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ አዲስ የውኃ ማጣሪያ ማሽን ተከለ፡፡ ማሽኑ በሰዓት 58 ሜትር ኪውብ ውኃ የማጣራት አቅም ያለው ሲሆን፣ ፋብሪካው ግን በአሁኑ ወቅት በሰዓት ከ30 እስከ 40 ሜትር ኩውብ ውኃ እያጠራበት እንደሚገኝ ሐሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. በተዘጋጀው የፋብሪካው የጉብኝት ፕሮግራም ላይ አስታውቋል፡፡ የበደሌ ቢራ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ አቶ መሰለ አምሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በሥራ ላይ የነበረው የውኃ ማጣሪያ ማሽን፣ ዘመን ያለፈበትና በተገቢው ደረጃ የመሥራት አቅም አልነበረውም፡፡ በዚህም ወደ አካባቢው የሚለቀቀው ጥቅም ላይ የዋለ ውኃ ጉዳት ይኑረው አይኑረው በውል የሚታወቅ ነገር አልነበረም፡፡ ይሁንና አዲስ የተተከለው ማጣሪያ ማሽን ውኃውን ሙሉ ለሙሉ በማጣራት ወደ አካባቢ እንደሚለቅና የሚለቀቀው ውኃም ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ችግር እንደማያስከትል የተረጋገጠ፣ ለእርሻ ሥራም መዋል ይችላል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ከፋብሪካው የሚወጣው ተረፈ ምርት ለማዳበሪያነት እንደሚውል ሲገልጹ፣ ‹‹በቀን አሥር ሜትር ኩብ የተጣራ ተረፈ ምርት ከፋብሪካው ይወጣል፡፡ ይኽም ለማዳበሪያነት የሚጠቅም ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲቀጠሙበት እያደረግን ነው፤›› በማለት አቶ መሰለ አብራርተዋል፡፡ ማሽኑ የፋብሪካውን የውኃ አጠቃቀም ፍጆታ 50 በመቶ በመቀነስ የውኃ ብክነትን ሊያስቀርለት ችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር አንድ ሊትር ቢራ ለማምረት አሥር ሊትር ውኃ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር፣ አሁን ግን አንድ ሊትር ቢራ ለማምረት ከአምስት ሊትር ያልበለጠ ውኃ እየተጠቀመ መሆኑንና በመጪዎቹ አራት ዓመታት ውስጥም ፋብሪካው የሚጠቀመውን የውኃ መጠን 85 በመቶ ለመቀነስና ለማኅበረሰቡ ለመመለስ እንደሚሠራ የሐይኒከን ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር፣ ጌሪት ቫንሉ ተናግረዋል፡፡ በ1985 ዓ.ም. በበደሌ ከተማ የተቋቋመው በደሌ ቢራ፣ በደሌ ፕሪሚየምና በደሌ ስፔሻል የተሰኙ ቢራዎችን እያመረተ ይገኛል፡፡ 250,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ፋብሪካው በወር ከ600 ሺሕ ሔክቶ ሊትር በላይ ቢራ የመጠቀም አቅም እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በደሌ ቢራ እ.ኤ.አ. በ2011 ለግዙፉ የኔዘርላንድስ ቢራ አምራች ኩባንያ ሐይኒከን በፕራይቬታይዜሸን መሸጡ ይታወሳል፡፡ ሐይኒከን በደሌ ቢራ ፋብሪካንና ሐረር ቢራን ከመንግሥት ከመግዛቱም ባሻገር፣ ቅሊንጦ አካባቢ በ110 ሚሊዮን ዩሮ ያስገነባው የሐይኒከን ቢራ ፋብሪካ በግዙፍነቱ ከሌሎች ቢራ ፋብሪካዎች ቀዳሚ ሆኗል፡፡ በበደሌ ሐረር ቢራ ፋብሪካዎች ከሚያመርተው 900 ሺሕ ሔክቶ ሊትር ባሻገር፣ በሐይኒከን ቢራ ፋብሪካ ብቻ በዓመት ከ1.5 ሚሊዮን ሔክቶ ሊትር ያላነሰ ቢራ ይጠምቃል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1590ዎቹ ሐይኒከን ኩባንያ በአሁኑ ወቅት ከ170 በላይ አገሮች ውስጥ ድርሻ አለው፡፡ በሜክሲኮ፣ በቻይና፣ በአፍሪካና በሌሎችም አኅጉራት ከሚገኙ የቢራ ፋብሪካዎች ጋር አብሮ እየሠራ ይገኛል፡፡ ሐይኒከን የበደሌ ቢራ ፋብሪካን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ ግዴታዎችን እየተወጣ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል በበደሌ ከተማ ከወራት በፊት በ5.6 ሚሊዮን ብር ወጪ ለበደሌ ሆስፒታል የማስፋፊያ ሥራ ሠርቷል፡፡ ሆስፒታሉ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልም ሌሎች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሠራ ይገኛል፡፡ በመጪው ዓመት በአንድ ሚሊዮን ብር በጀት አንድ አምቡላንስ ገዝቶ ለሆስፒታሉ እንደሚያስረክብ ይፋ አድርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች