Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለሪዮ ኦሊምፒክ ከአትሌቶች ጋር የሚሄደው ልዑክ ታወቀ

ለሪዮ ኦሊምፒክ ከአትሌቶች ጋር የሚሄደው ልዑክ ታወቀ

ቀን:

– ውኃ ዋናና ብስክሌትን ጨምሮ 38 አትሌቶች ይሳተፋሉ

በብራዚል የሪዮ ደጄኔሮ ከተማ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለ17 ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው 31ኛው ኦሊምፒያድ የዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ውኃ ዋናና ብስክሌትን ጨምሮ 38 አትሌቶች በውድድሩ እንደሚሳተፉ ገልጿል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በራማዳ አዲስ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተለያዩ የመንግሥት አመራሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ60 በላይ የልዑካን ቡድን ወደ ብራዚል የሚያቀና እንደሆነ የኦሊምፒክ ኮሚቴው ዋና ጸሐፊና የቡድን መሪው አቶ ታምራት በቀለ ተናግረዋል፡፡ ተሳታፊ አትሌቶችን አስመልክቶም በውኃ ዋና በአንድ ወንድና በአንድ ሴት፣ በብስክሌት ደግሞ በአንድ ወንድ፣ እንዲሁም በአትሌቲክስ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ከተጠባባቂዎቹ ጋር 35 አትሌቶች በሪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊዎች ይሆናሉ፡፡ አሠልጣኞችን፣ ወጌሾችና የቡድኑን ሐኪሞች ጨምሮ 22 የልዑካን ቡድኑ አባል እንዲሆኑ መደረጉን ጭምር ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ እንደ ኃላፊው ቁጥሩ በዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚጋበዙ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችንና ጋዜጠኞችን እንዲሁም በራሳቸው ተነሳሽነት ከልዑካን ቡድኑ ጋር አብረው የሚጉዙትን እንደሚያካትት በጋዜጣዊ መግለጫው ተብራርቷል፡፡ በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተመለከተው፣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አልባሳት ለማዘጋጀት እንዲሁም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውን በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች ማገዝና መደገፍ ለሚፈልጉ ከ60 በላይ ኩባንያዎችና ድርጅቶች አርጄ በተሰኘ ድርጅት አማካይነት ማብራሪያ ተደርጓል፡፡ እስካሁንም በርካታ ኩባንያ ድርጅቶች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውም ተገልጿል፡፡ የገቢ አሰባሰቡን ሒደት አስመልክቶም እንዳለፉት ዓመታት ዓይነት ቋሚ ፕሮግራም በማዘጋጀት እንዳልሆነና እያንዳንዱ ኩባንያና ድርጅት አሠራሩና ሒደቱ ባለበት ቦታ እንዲብራራለት በማድረግ እንደሆነም ዋና ጸሐፊው አቶ ታምራት አብራርተዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑን አልባሳት አስመልክቶም ባለፉት ዓመታት ከነበረው ብሔራዊ አልባሳት ለየት እንዲል ተደርጎ ስለመዘጋጀቱም አቶ ታምራት ተናግረዋል፡፡ ይኼውም አትሌቶች በሽልማት ወቅት፣ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ በዝግጅትና በኦሊምፒክ መኖሪያ ካምፕ ወቅቶች የሚለብሱት አልባሳት መሠረታዊውን የአገሪቱን መለያ መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን ጭምር ተናግረዋል፡፡ ከብሔራዊ አትሌቶች መካከል አልማዝ አያና፣ ደጀን ገብረመስቀል፣ ገለቴ ቡርቃና መሐመድ አማን በጋዜጣዊ መግለጫው የተገኙ ሲሆኑ፣ ሁሉም ጥሩ ዝግጅት እንዳደረጉ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያውያን የምንግዜም ተቀናቃኝ ከሆኑት ኬንያውያን አትሌቶች መካከል ቪቪያን ቸሪዮት በረዥም ርቀት በወቅታዊ ብቃቷ ከወዲሁ ብዙ እየተባለባት ስለሚገኘው ስለአልማዝ አያና ተጠይቃ ‹‹አልፈራትም›› ማለቷን ተከትሎ ለአልማዝ አያና ጥያቄ ቀርቦላት ‹‹መድረኩ ይለየናል›› ብላለች፡፡ በመጨረሻም ወደ ብራዚል የሚያቀናው የኢትዮጵያ ልዑካን የአገሪቱን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መወከል የሚችል በማፊ ዲዛይን የተዘጋጀ የአገር ባህል ልብስ እንደተዘጋጀለትም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...