አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ • 1 ኪሎ ግራም የጭቅና ሥጋ • ሩብ ሊትር የእንጉዳይ ሶስ • 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ • 1 የሻይ ማንኪያ ጨው አዘገጃጀት 1. ሥጋውን በወፍራሙ አሥር ቦታ መከፋፈል፤ 2. ቅቤውን መጥበሻ ላይ አድርጐ ማሞቅ፤ 3. ሥጋውን በጨውና በቁንዶ በርበሬ መለወስ፤ 4. መጥበሻው ላይ አገላብጦ መጥበስና በጣም ሳይበስል ማውጣት፤ 5. የእንጉዳይ ሶሱን አንተክትኰ ማውጣት፤ 6. ሶሱን የተጠበሰው ሥጋ ላይ በስሱ መቀባትና ማቅረብ፡፡ – ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)