Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

‹‹አማርዝኛው›› ብሔራዊ የቱሪዝም መለያ የ13 ወር ፀጋን ተክቷል

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ቱሪዝም ከአራት ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ ገቢ አስገኝቷል ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አገልግሏል፡፡

የአገሪቱን የቀን አቆጣጠር ልዩነት ብቻም ሳይሆን ያሏትን የአየር ንብረት ይዘቶች በማስተዋወቅ ረጅም ዘመናትን አስቆጥሯል፡፡ ይሁንና በአዲስ የሚተካበት ጊዜ በመምጣቱ ምክንያት ሌላ የቱሪዝም መለያ ምልክት ሲፈለግ ቆይቷል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲዘጋጅ ቆይቶ፣ ወደ ተግባር እስኪመጣም አንድ ዓመት አስቆጥሮ በመጨረሻው ለሕዝብ ይፋ ተደርጓል፡፡ ከእንግዲህም አገሪቱ ለዓለም የቱሪዝም ገበያ የምትተዋወቀው በአዲሱ መለያ ምልክቷ ይሆናል፣ የዓለም ቱሪዝም ገበያዎች ላይም በአዲሱ ስሟ ኢትዮጵያ ትሸጣለች ያሉት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ናቸው፡፡

አቶ ተወልደ ስለ አዲሱ ብሔራዊ የቱሪዝም መለያ ሲያብራሩም፣ ገላጭ የሆነባቸውን ነጥቦች ዘርዝረዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ላንድ ኦፍ ኦሪጅንስ›› በሚለው መግለጫ ወይም መፈክር፣ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የተጻፈው ከአማርኛ ወይም ከግዕዝ ፊደላትና ከእንግሊዝኛ ፊደላት ጋር ተዳቅሎ የተወለደ ሲሆን፣ ‹‹አማርዝኛ›› ወይም አማርኛ-እንግሊዝኛ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የፊደላቱ በዚህ መንገድ መፈጠር ከወዲሁ ጥሩ ተቀባይነት አስገኝቷል፡፡ ‹‹የብዙዎች መገኛ ምድር›› የሚል ዓይነት አማርኛዊ ፍች ሊሰጠው የሚችለው ‹‹ላንድ ኦፍ ኦሪጅንስ›› የሚለው አገላለጽ ግን ኦፊሴላዊ የአማርኛ ፍች ገና አልተዘጋጀለትም ተብሏል፡፡ የብዙዎች መገኛ ምድር ወይም ላንድ ኦፍ ኦሪጅንስ ለሚለው መግለጫ ቢያንስ ሦስት መሠረታዊ ማብራሪያዎች የቀረቡ ሲሆን፣ የሰው ዘር መገኛነቷን፣ የዓለም ተፈላጊው መጠጥ የቡና ምድርና መገኛነቷን እንዲሁም ዓባይ ወንዝን ጨምሮ የባህል፣ የልዩ ልዩ ብሔሮችና ሕዝቦች ማደሪያነቷን ከገላጭ ቃላቱ ባሻገር በዛፍ ምሥሉ ለመከሰት ተሞክሯል፡፡ አቶ ተወልድ ባደረጉት ገለጻ መሠረት፣ የኢትዮጵያን ማንነት ይገልጻል የተባለው ዛፍ በቀለማቱ፣ በሥሮቹና በግንዶቹ እንዲሁም በቅጠሎቹ ብዙ ይናገራል፡፡

የቱሪዝሙን ዓርማ ወይም መለያ የውጭ ድርጅቶች ያዘጋጁት ስለመሆኑ የተገጸበት ሒደት፣ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች መለያ ጋር መነጻጸሩን፣ እንደ ቱርክ ከመሰሉ አገሮች መነሻ ተሞክሮ መወሰዱን ስለ መለያው የተከተቡ ጽሑፎች ያጣቅሳሉ፡፡ የአገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻዎች ይበልጥ ለዓለም ገበያ የሚያስተዋውቀው ይህ መለያ ብቻም ሳይሆን በአገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው የሆቴል ኢንቨስትመንት ወደ ፊት እንደ ማይክሮሶፍት፣ አይቤኤም፣ ጄነራል ሞተርስ የመሳሰሉ ትልልቅ ኩባንያዎች ዓመታዊ ጉባዔዎቻቸውን ሲያካሂዱ ከሚሰበሰቡባቸው አገሮች ተርታ ኢትዮጵያም አንዷ እንድትሆን ወደፊት የሚሠሩ በርካታ ሥራዎች እንደሚኖሩ አቶ ተወልደ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህም በሻገር ለጎብኚዎች ቀላል የቪዛ አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ በኢንተርኔት እንዲሁም በድረ ገጽ አማካይነት አገልግሎት ለመስጠት አየር መንገዱ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮችና ከሌሎችም መሥሪያ ቤቶች ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ ከአሥር ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ከአምስት የአፍሪካ የቱሪስት መዳረሻ አገሮች አንዷ እንድትሆን ቱሪዝም ሚኒስቴር አቅዷል፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላም አገሪቱን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 2.2. ሚሊዮን እንደሚሆን ይታሰባል፡፡ ይሁንና ይህ አኃዝ ወደ አምስት ሚሊዮን መሻሻል እንደሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ ሰሞኑን በተካሄደው የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ጉባዔ ላይ ባሳሰቡት መሠረት ወደ አምስት ሚሊዮን እንዲያድግ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ ይህንን ማድረግ በቀላሉ እንደሚቻልም አቶ ተወልደ ይስማማሉ፡፡ ችግሩ ግን የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብዛትና ጥራት ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑ ነው የሚሉት አቶ ተወልደ፣ በሆቴል፣ በሎጅና በሪዞርት ግንባታ ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው የፋይናንስ አስተዳዳሪ ሆኖ የዓለም ባንክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ፋይናንስ አቅራቢዎች ለማበደር ፍላጎት እንዳላቸው አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና በተያዘው ዓመት ወደ አገሪቱ ይመጣሉ ተብለው ከተገመቱ አንድ ሚሊዮን ጎብኝዎች መካከል 910 ሺሕ በመምጣታቸው ትልቅ ውጤት ሲገኝ፣ በገቢ ደረጃም ከአራት ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ የውጭ ምንዛሪ ሊገኝ መቻሉን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከፋይናንስ ባሻገርም መንግሥት ለሆቴልና ለሎጂ ግንባታ የሚውል መሬት ለአልሚዎች እንደሚከልል አቶ ኃይለ ማርያም አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ክልሎች በቱሪስት መዳረሻ አካበቢዎች ለሚካሄዱ የሆቴልና መሰል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ የሚውል ቦታ እንዲከልሉ መመርያ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች