Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ማሻቀብ የአገሪቱን ዕዳ የመክፈል አቅም እንደሚጎዳ ፊች የተባለው...

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ማሻቀብ የአገሪቱን ዕዳ የመክፈል አቅም እንደሚጎዳ ፊች የተባለው ድርጅት አስታወቀ

ቀን:

ከሁለት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ የመሸከም አቅም እንዲገመግም በመንግሥት ተቀጥሮ የነበረው ፊች የተባለው የመበደር አቅም ምዘና ኤጀንሲ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዕዳ እያሻቀበ መሆኑንና በአገሪቱ ዕዳ የመክፈል አቅም ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል አስታወቀ፡፡ ፊች የተባለው ኩባንያ ረቡዕ ሐምሌ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የ2009 ዓ.ም. በጀትን በመገምገም በጥንቃቄ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጾ፣ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ግን በማሻቀብ ላይ መሆኑንና ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታትም መጨመሩን ይቀጥላል የሚል ግምት እንዳለው አስታውቋል፡፡ በአገሪቱ ሥርዓት መሠረት በርካታ ፕሮጀክቶች ከበጀት ወጪ ሆነው ተግባራዊ የሚደረጉት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች መሆኑን የሚገልጸው የድርጅቱ መግለጫ፣ ግዙፍ የሚባሉ የአገሪቱ ፕሮጀክቶች ከኃይል ማመንጫ እስከ ትራንስፖርትና የንግድ ሥራዎች ድረስ በእነዚህ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እንደሚከናወኑ ያትታል፡፡ በአገሪቱ አመራሮች የተለጠጡ ዕቅዶች በተለይም በኃይል ማመንጨትና በመሠረተ ልማት ግንባታዎች ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርጉት የልማት ድርጅቶች መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ በዚህ የተነሳ የእነዚህ ድርጅቶች ዕዳ እ.ኤ.አ. በ2015 መጨረሻ ማለትም በታኅሳስ 2008 ዓ.ም. ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 29 በመቶ እንደደረሰ ጠቁሟል፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት (GDP) 1.2 ትሪሊየን ብር መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በመሆኑም የአገሪቱን ዕዳ የመክፈል አቅም ለመገምገም፣ የእነዚህ ድርጅቶችን የዕዳ መጠን መከታተልና እንደ ቀጣይ የአገሪቱ ዕዳ አድርጐ እንደማያይ ድርጀቱ ገልጿል፡፡ የአገሪቱን ዕዳ የመክፈል አቅም በመጨው ጥቅምት ወር እንደሚገመገም ይፋ አድርጓል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አረዳ፣ ‹‹የተጋነነ ሥጋት ቢሆንም፣ ነገር ግን ሥጋቱን ማንሳታቸው ተገቢ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚባሉት እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትዮ ቴሌኮም መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ ለእነዚህ ድርጅቶች ብድር አቅራቢዎች ተራኩተው ብድር የሚያቀርቡት የመክፈል አቅም እንዳላቸው በመገንዘባቸው ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች አገሮች ደመወዝ ለመክፈል ወይም ለፍጆታ ብድር ውስጥ እንደማትገባ ያስረዱት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ጥያቄ ከተነሳም ለመሠረተ ልማት በምንበደረው ላይ ነው፡፡ ማለትም ለኃይል ማመንጫ ግድቦችና ለባቡር ፕሮጀክቶች፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡ በዋናነት ግን እንደ ዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) የመሳሰሉ ተቋማት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚባሉትን እንደማይወዷቸው፣ ይህ የሚመነጨውም ከርዕዮተ ዓለም ልዩነት የተነሳ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ያ ማለት ግን ሁኔታዎችን እየፈተሽን አንሄድም ማለት አይደለም፡፡ በጥንቃቄ ነው ወደ ብድር የሚገባው፡፡ ስለዚህ አሳሳቢ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ መንግሥት በይፋ የእነዚህ ድርጅቶች የዕዳ መጠን አሳሳቢ እንደሆነ ባይናገርም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የልማት ድርጅቶች ብድር የመቀነስ አዝማሚያዎች እያሳዩ ይመስላሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል መንግሥት በ2009 ዓ.ም. በጀት ውስጥ ትልቅ ትኩረት ከሰጣቸው መካከል በሦስተኛ ደረጃ የሚገኘው ዕዳ ክፍያ ሲሆን፣ 13 ቢሊዮን ብር ለዚህ በጀት ዓመት ተይዞ ፀድቋል፡፡ ከኃይል ልማት አንፃር በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 18,899 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት ዕቅድ ውስጥ 13,358 ሜጋ ዋት በግል ባለሀብቶች እንዲለማ ተወስኗል፡፡ በዚሁ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ የተካተቱ አገር አቀፍ የባቡር ፕሮጀክቶችም በግል ባለሀብቶች እንዲገነቡ መወሰናቸውን፣ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጥናት እያካሄደ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...