Thursday, February 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርኪስ አውላቂዎች ሆይ ሰነዶቼን መልሱልኝ

ኪስ አውላቂዎች ሆይ ሰነዶቼን መልሱልኝ

ቀን:

ግንቦት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ገደማ በ23 ቁጥር አውቶብስ ለመሳፈር ተጓዡ ቲኬት ለመቁረጥ በተሠለፈበት ጊዜ፣ ድንገተኛ በሚመስል አኳኋን ጭንቅንቅ ፈጥራችሁ፣ ገንዘብና ልዩ ልዩ ሰነድ የያዘውን ቦርሳዬን በመውሰድ በሠለጠነ እጃችሁ ያደረሳችሁብኝ በደል ላስታውሳችሁ እወዳለሁ፡፡ የሠለጠነው እጃችሁ ግዳጁን የፈጸመው ወደ አውቶብሱ ሳልገባ ነው፡፡ መሰረቄን ባወቁት ጊዜም በዚያ ሰፊ ሜዳ ላይ ተጨናንቆ ከተሰበሰበው ሕዝብ መካከል የወሰደብኝን መለየት አልቻልኩም፡፡ ጥርጣሬም እንደማያዋጣ አወቅሁ፡፡ የነበረኝ አማራጭ ለፖሊስ ማመልከት ብቻ ሆነ፡፡ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኘው መስኪድ አካባቢ መሆኑ ስለተነገረኝ ወደዚያ በማምራት አንዲት የፖሊስ አርማ ምልክት ወደ ተደረገባት ቤት አመራሁ፡፡ እዚያ ላገኘሁት የፖሊስ ባልደረባም የደረሰብኝን ነገር አስረዳሁ፡፡ ‹‹እኔ የምረዳህ ነገር ስለሌለ ወደ ጣቢያ ሂድ አለኝ፡፡ በዚህ ምላሹ ቅር ስለተሰኘሁ ታዲያ እዚህ የምትሠራው ምንድነው ብዬ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ፡፡ እሱ ግን ይሄ እኮ ፖሊሶች ሲደክማቸው የሚያርፉበት እንጂ ጣቢያ አይደለም ብሎኝ አረፈው፡፡ ይህ በመሆኑም ቀድሞ ወደ ማውቃቸው፣ ወደ አራተኛ ጣቢያ ባልደረቦች አመራሁ፡፡ በቦታ ስደርስ ግን ጣቢያውን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ የለም፡፡ የት ሄደ ብል ወደ ኳስ ሜዳ ተዛውሯል ተባልኩ፡፡ ከቀድሞው አራተኛ ጣቢያ ኳስ ሜዳ መጓዝ ለእኔ በጣም ሩቅ ነው፡፡ ታክሲ ማግኘት አይቻልም፡፡ ግዴታዬ ሆነና ግን በእግሬ ተጉዤ እንደምንም ወደ ጣቢያው ደረስኩ፡፡ በጣቢያ ስደርስ በርከት ያሉ የፖሊስ አባሎች ቦታ ቦታቸውን ይዘው ወደ ተቀመጡበት ቢሮ በመግባት በመካከላቸው ቆሜ የደረሰብኝን ባጭሩ ገልጬ ጉዳዩ ወደሚመለከተው እንዲመሩኝ ጠየቅሁ፡፡ ከተቀመጡት መካከል አንዷ ፖሊስ ምስክር አለህ ወይ ብላ ጠየቀችኝ፡፡ እኔም በጥያቄው በመደነቅ ጭርሱኑ የምስክርነት ትርጉሙ ጠፋብኝ፡፡ ‹‹የእኔ እኮ አቤቱታ ሌባ ሰረቀኝ ነው እንጂ እገሌ የሚባል ወሰደብኝ የሚል አይደለም፡፡ ሌብነት ምን ማለት እንደሆነ ለፖሊስ ለማስረዳት ከእኔ የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ የወሰደብኝን ባውቅማ ምስክር ከመቁጠር ንብረቴን አላስመልመስም ነበር ወይ?›› በማለት ጥያቄዋን በጥያቄ መለስኩላት፡፡ እንዲያ ከሆነ ማመልከቻ ጻፍና ክሰስ በማለት ቀጭን ምላሽ ሰጠችኝ፡፡ በእኔ ሞት ማን ብዬ ማንን ይሆን የምከሰው፣ ‹‹እገሌ ብዬ የምከሰው የለኝም፤›› አልኳት፡፡ በዚህ ጊዜ በአቅራቢያው የነበሩ ፖሊሶች አሠራራችን ይኸው ነው አሉ፡፡ ይህን በመነጋገር ላይ ሳለን አንዲት ፖሊስ ከሌላ ክፍል መጥታ ጉዳዬ ምን እንደሆነ ስለጠየቀችኝ ወደ ማስረዳቱ ገባሁ፡፡ እሷም ግን እኔን የዘረፋ ወንጀል እንጂ ይህ አይመለከተኝም ብላ ሄደች፡፡ በልቤ ከዘረፋስ ይሰውረኝ አልኩና ወደ ፖሊሶች መለስ ብዬ የጠፋብኝን ንብረት እንደማላገኘው እርግጠኛ ነኝ ግን የቀበሌ መታወቂያዬ አብሮ ስለተወሰደብኝና ያለመታወቂያ መንቀሳቀስ ስለማችል ምን ላድርግ ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ እነሱም ይኼ ችግር እንደሌለው፣ አሥር ብር ከፍዬ ለምትኖርበት ቀበሌ እንደሚጽፉልኝ ገለጹልኝ፡፡ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ፤›› የሚል ጽሑፍና አርማ ባለበት ደረሰኝ በሴሪ ቁጥር 735502 መሠረት አሥር ብር ክፍዬና ቀላጤ ተጽፎልኝ፣ በባለሥልጣን ተፈርሞበትና ማኅተም ተደርጎበት ደረሰኜ ተሰጠኝና ተሰናበትኩ፡፡ ፖሊስ ቀላጤ ለጻፈበት አሥር ብር፣ ለፎቶግራፍ፣ ለቀበሌ መታወቂያ መለወጫ ወይም ለተሰረቀብኝ መቀየሪያ ከፍዬ አዲስ መታወቂያ አወጣሁ፡፡ ለፖሊስ አመልክቼ ያገኘሁት ውጤት በስተመጨረሻው ይኼው ብቻ ነው፡፡ ለፖሊስ ያመለከትኩበት አንዱ ምክንያት ‹‹ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም፤›› እንደሚባለው ምናልባት፣ ገንዘቤን ስትካፈሉ ጠብ ተፈጥሮ ፖሊስ ቢደርስ ድርጊታችሁ ተጋልጦ ንብረቴን አገኛለሁ ብዬ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ እንግዲህ ኪስ አውላቂነት ወንጀል መሆኑ በፖሊስ ዘንድ ካልታወቀ ዘንድና፣ ክትትል ይደረግብናል ብላችሁ አትስጉ፡፡ የፖሊስ ጉዳይ በዚህ ከተዘጋ፣ እናንተም ለእኔ እዘኑልኝ፡፡ የሚጠቅማችሁ ገንዘቡ ብቻ ስለሆነ በቦርሳዬ ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ሰነዶችና የቤተሰብ ፎቶግራፎች (መተኪያ የሌላቸው) ስለማይጠቅሟችሁ እዚያው በምታገኙት አድራሻ መሠረት ቤቴ መጥታችሁ ግቢው ላይ ጣል አድርጋችሁልኝ ብትሔዱ ምናለበት፡፡ ወ/ሮ ሸዋዬ፣ ከአዲስ አበባ **** ፉቶን መኪና የቻይና ብራንድ ነው ‹‹ዓባይ ቴክኒክና ንግድ ኩባንያ በሃያ ሚሊዮን ብር ካፒታል የንግድ መኪኖችን መገጣጠም ጀመረ፤›› በሚል ርዕስ፣ ሪፖርተር በረቡዕ የሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ዕትሙ ቢዝነስና ኢኮኖሚ አምድ ላይ የወጣውን ዘገባ ማስነበቡ ይታወሳል፡፡ በዚህ ዘገባ ‹‹…የጀርመን ብራንድ የሆነውንና ፉቶን የተሰኘው ኩባንያ ያመረታቸውን ሚኒባሶችና ፒክአፖች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፤›› የሚል ዓረፍተ ነገር ተካቷል፡፡ ይሁንና የጀርመን ብራንድ ተብሎ የተገለጸው ፉቶን መኪና የቻይና ምርት በመሆኑ፣ ለተፈጠረው ስህተት አንባብያንና ኩባንያውን ይቅርታ በመጠየቅ በተገለጸው መሠረት ተስተካክሎ እንዲነበብ እንጠይቃለን፡፡ (ከዝግጅት ክፍሉ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...