Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጎንደር ከተማ በፀጥታ ኃይሎችና በነዋሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ...

በጎንደር ከተማ በፀጥታ ኃይሎችና በነዋሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ አደጋ መድረሱ ተጠቆመ

ቀን:

በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በነዋሪዎች መካከል ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ በተከሰተ ግጭት ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቆመ፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ግጭቱ የተነሳው ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሚፈለግን አንድ ግለሰብ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ንጋት ላይ ለመያዝ ሲሞክሩ፣ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው ደሳለኝ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች በመቃወማቸው ነው፡፡ በዚህም ከሁለቱም ወገኖች ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል የሚናገሩ አሉ፡፡ የፌዴራልና የአርብቶ አደሮች ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ወርቄ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት የፈጠረው ቡድን ማንነት፣ መነሻው ምክንያትና የደረሰው ጉዳት መጠን በፌዴራል ፖሊስ ገና በመጣራት ላይ እንዳለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ባለኝ መረጃ የሰው ሕይወት አልጠፋም፤›› ብለዋል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱትን ዕርምጃ የተቃወሙ ግለሰቦች ሐምሌ 5 ቀን ከቀትር በኋላ የሰላም ባስን እንዳቃጠሉ አረጋግጠዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሪፖርተር ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን፣ ‹‹መረጃው ገና እየተጠናቀረ ነው፤›› የሚል ምላሽ አግኝቷል፡፡ ግጭቱ ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ በመሆኑ በአካባቢው በሚገኙ በጎንደርና በትግራይ ተወላጆች ግንኙነት ላይ መጥፎ አሻራ ጥሎ እንደሚያልፍ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ አቶ አበበ ግን ‹‹ጉዳዩ ከወልቃይትና ጠገዴ ጥያቄ ጋር መገናኘቱን ገና አላረጋገጥንም፤›› ብለዋል፡፡ ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ግን፣ በዕለቱ ኤርትራ ውስጥ መሽገው ከሚገኙ የፀረ ሰላምና አሸባሪ ኃይሎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠርና መመርያ በመቀበል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ሶሮቃና ቁርቢ አካባቢ እንዲሁም ትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳ ደንሻና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ ግብረ ኃይሉ ግለሰቦቹ በአካባቢው የሚያልፉ የሕዝብና የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ተኩስ በመክፈት ጥቃት በመፈጸም የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርጉ እንደነበርም ጠቅሷል፡፡ መግለጫው ግብረ ኃይሉ ከፍርድ ቤት መያዣ በማውጣት ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. አብዛኛዎቹን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ያመለክታል፡፡ ይሁንና ከመካከላቸው ሁለት ተጠርጣሪዎች ግብረ ኃይሉ ላሰማራቸው የፀጥታ ኃይሎች እጅ ላለመስጠት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን ከለላ በማድረግ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ላይ የመሣሪያ ተኩስ በመክፈትና ቦምብ በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸውን አስታውቋል፡፡ የጉዳቱ መጠን ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም ገልጿል፡፡ የፋና ዘገባ ግጭቱ የተፈጠረውና ተጠርጣሪዎች በቁጥር ሥር የዋሉት ጎንደር ከተማ ውስጥ ስለመሆኑ ያለው ነገር የለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...