Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ከ70 በላይ ተማሪዎች ትምህርት ሊጀምሩ ነው

  ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ከ70 በላይ ተማሪዎች ትምህርት ሊጀምሩ ነው

  ቀን:

  ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የተከሰተውን ብሔር ተኮር ግጭት በመፍራት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ትግራይ ክልል ሄደው የነበሩ ከ70 በላይ ተማሪዎች ትምህርት ሊጀምሩ መሆኑ ተነገረ፡፡

  በተፈጠረው ግጭት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በማቋረጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው የነበሩ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ሰሞኑን ትምህርት እንደሚጀምሩ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ማክሰኞ ጥር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

  ግጭቱን በመፍራት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ትግራይ ክልል ሄደው የነበሩ ቁጥራቸው 75 እንደሆነ ያቋረጡ ተማሪዎች ተወካዮች ለሪፖርተር ቢጠቁሙም፣ ወ/ሮ ሐረጓ ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን አቋርጠው የመጡት ምግብና መጠለያ ትምህርት ሚኒስቴር ለአራት ቀናት ያህል ሲሸፍንላቸው እንደቆየ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ድጋፉ ተቋርጦ ወደ ዩኒቨርሲቲያችሁ ግቡ በመባላቸው ሳቢያ ባለመስማማት ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄዳቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

  ዋና ዳይሬክተሯ እንደናገሩት፣ ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት ተደርጎ መግባባት በመፈጠ፣ መኪና ተልኮላቸው ማክሰኞ ጥር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው ሄደዋል፡፡

  ግጭቱን በመፍራት ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብዛት ያላቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው እንደወጡ መረጃዎች ቢያሳዩም፣ ከዩኒቨርሲቲው አመራር ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

  ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲግራት ዩኒቨርሲቲና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ግጭት መቀስቀሱ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በወቅቱ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የአንድ ተማሪ ሕይወት ሲጠፋ፣ በወለጋና በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች የሦስት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን፣ በ19 ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ትምህርት መቋረጡን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. የመከላከያ ሚኒስትርና የፌዴራልና የክልሎች የጋራ የፀጥታ ምክር ቤት ሴክሪታሪያት ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ሙሉ በሙሉ ወደ ማስተማር ሥራቸው እንዳልገቡ መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አቶ ሲራጅ ይህን ቢሉም፣ ወ/ሮ ሐረጓ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ማስተማር ሥራቸው መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

  ወ/ሮ ሐረጓ ግጭት በመፍራት ወደ ትግራይ ክልል ሄደው ከነበሩት ጋር ውይይት ተደርጎ ለመመለስ ፈቃደኛ መሆናቸውን ከመግለጽ በላይ፣ በሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

  ከግጭቱ ጋር ተያይዞ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ ተማሪዎች በሕግ ጥላ ሥር መዋላቸውን አቶ ሲራጅ መናገራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ሪፖርተር ባገኘው መረጃ መሠረት የወልዲያ፣ የአዲግራትና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የተጠረጠሩ ተማሪዎችን በቁጥጥር ሥር ካዋሉ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...