Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የዘንድሮ ፊቼ ጨንበላላ

ትኩስ ፅሁፎች

የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጨንበላላ በዓል ከሰኔ 21 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. የተከበረው እንደወትሮው ሁሉ በአገር ሽማግሌዎች ሞራ በማንበብና በምርቃት ነበር፡፡ በዓሉ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን በማስመልከት የብሔሩ ተወላጆች፣ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ደስታቸውን በተለያየ መንገድ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የሲዳማ ዘመን መለወጫ የፊቼ ጨንበላላ በዓል በዩኔስኮ የተመዘገበበትን ሰርተፊኬት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ለአቶ ደሴ ዳልኬ በማስረከብ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

ፎቶ በታምራት ጌታቸው

ስህነ አንስቲያ
                                                                                                                                                                                                   አንቺ ባለ ጥበብ ÷ ጥበብሽ የሚያምር
ስህነ  አንስቲያ ÷ ፈትለ ወርቅ ወብሩር
በጥሩ ቍመናሽ ÷ በወርድ መሥፈርትሽ ልክ
እንዴት ልዩ አድርጎ ÷ ቢሠራው እግዜር
ያውጣሽ! ያውጣሽ! ያሉሽ ÷ ከክፉ ነገር።
የተድላ የደስታ ÷ የፍቅር መጠለያ
የትሕትና አዳራሽ ሳለሽ ምድረ ሓበሻ
አዎን እርሱ ያውጣሽ! እስከ መጨረሻ
ካበጃጀሽ ወዲያ ÷ ያሣመረሽ ነሻ።
የጥበብ መዋያ ÷ ውቀት ዓለም ማያ
የሥልጣኔ ዓውድ ÷ የብዝሃነት ማጕያ
አንቺ እንጂ ማን አለ? ሀገሬ ኢትዮጵያ
ከወደደሽ ዘንዳ ÷ ካፈቀረሽ በያኽ።
                        ኃይለ ልዑል ካሣ
                            አዲስ አበባ
                  ግንቦት 20 ቀን 2008 .ም.

*****

ሁለተኛዋ የእንግሊዝ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር

የእንግሊዝ ሁለተኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ረቡዕ ሐምሌ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚሾሙት ቴሬሳ ሜይን መገናኛ ብዙኃን ከማርጋሬት ታቸር ጋር እያነፃፀሯቸው ነው፡፡ ቴሬሳ ከጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጋርም የሚመሳሰሉበት ነገር አለ፡፡ ሁለቱም በሚያምኑበት አቋም የሚፀኑ ትችታቸውን ለመሰንዘርም ወደ ኋላ የማይሉ ናቸው፡፡ ሁለቱም የካህን ልጆች ሲሆኑ ደረጃ በደረጃ ከታች ጀምረው የአገራቸው መሪ መሆን የቻሉ ናቸው፡፡ በማንኛውም ጊዜ ሜርክልና ቴሬሳ መልካም የሥራ ግንኙነት ያላቸው ቢሆንም በእንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት መውጣት ማግስት ሜርክል ኅብረቱን መልቀቅ ቀላል እንደማይሆን እንግሊዝን ቴሬሳንም እያስጠነቀቁ ነው፡፡ ‹‹ከእንግሊዝ ጋር የሚኖረን ድርድር ከባድ ይሆናል›› ያሉት ሜርክል እንግሊዝ በቀጣይ ከኅብረቱ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ምን ዓይነት እንዲሆን እንደምትፈልግ በፍጥነት ማሳወቅ እንዳለባት ገልጸዋል፡፡

******

የደም ለጋሾች ጾታና ዕድሜ በተቀባዩ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል

ሰኞ ይፋ የሆነው የአሜሪካ ሜዲካል አሶሴሽን ጆርናል እንደሚያሳየው የደም ለጋሾች ጾታና ዕድሜ በተቀባዮች ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡ በዚህም ከወጣትና ሴት ለጋሾች የሚገኝ ደም በተቀባዩ ዘንድ የሚያስገኘው ውጤት እስከዚህም ነው ተብሏል፡፡ ከወጣት ሴትም ወንድም ደም ለጋሾች የተገኙ ደሞችን ውጤታማነት ያጠኑት ተማራማሪዎች ዕድሜያቸው ከ 17 እስከ 20 ከሆኑና ከ40 እስከ 50 ከሆኑ ለጋሾች ደም ያገኙ ሕመምተኞችን ጤንነት በማነጻጸር ከወጣቶቹ የተወሰዱት ስምንት በመቶ ከፍ ያለ ለሞት ተጋላጭነት አላቸው ብለዋል፡፡

******

የስፔኑ ኮርማ ተዋጊ በኮርማ ተገደለ

ታዋቂው የእስፔኑ ኮርማ ተዋጊ የ29 ዓመቱ ቪክቶር ባሪዮ በርካቶች በተሰበሰቡበት እየታገለው በነበረው ኮርማ ተገደለ፡፡ በስፔን የኮርማ ትግል የተለመደ ዓይነት ስፖርትና ትርኢት ሲሆን በአገሪቱ በትርኢቱ ላይ የኮርማ ተዋጊ ሲሞት ከ30 ዓመታት ወዲህ ባሪዮ የመጀመሪያው እንደሆነ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው፡፡ ይህን አሠቃቂ ሁኔታ የተከሰተበት ትርኢትን ይከታተሉ ከነበሩት የ32 ዓመቷ የባሪዮ ባለቤት ሪኩዌል ሳንዝም አንዷ ነበረች፡፡ ባሪዮ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ዶክተሮች ሕይወቱን ሊያተርፉ አልቻሉም፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች