ወፎች በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት በላባቸው ይለያሉ፡፡ ከ9,800 በላይ የወፍ ዓይነቶች ሲኖሩ፣ መጠናቸውም ከ2.1/4 ኢንች ከምትሆነው ሂዩማኒንግ አንስቶ እስከ ዘጠኝ እግር ርዝመት እንዳላት ሰጐን ይደርሳሉ፡፡ ክብደታቸው ቀላል ቢሆንም፣ ጠንካራ አጥንት አላቸው፡፡ መደባቸውም የጀርባ አጥንት ካላቸው እንስሳት ነው፡፡
የወፎች ክንፎች እንደየወፎቹ ዝርያዎች ያድጋሉ፡፡ ከወፍ ዝርያዎች ክንፍ አልባዎቹ ኤሌፋንት እና ኤክስቲንክትሞስ የተባሉት ናቸው፡፡
ወፎች ዕውቀታቸውን በማስተላለፍ ይታወቃሉ፡፡ ብልህም ናቸው፡፡ ኮርቪድስ እና ፓሮት (በቀቀን) ከሁሉም ዝርያዎች በብልህነታቸው ይታወቃሉ ሲል ናሽናል ጆግራፊ በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡