Sunday, April 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበፖላንዱ የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና 25 አትሌቶች ይሳተፋሉ

በፖላንዱ የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና 25 አትሌቶች ይሳተፋሉ

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድር ዓመቱ ከሚሳተፍባቸው አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በፖላንድ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 12 እስከ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ የሚካሄደው የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይጠቀሳል፡፡ በሻምፒዮናው የሚሳተፉ 25 አትሌቶች ሐምሌ 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ሥፍራው እንደሚያመሩ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

የአንድ ወር ዕድሜ ለቀረው የሪዮ ኦሊምፒክ ከመካለኛው ርቀት እስከ ማራቶን መሳተፍ የሚያስችለውን ዝግጅት እያከናወነ የሚገኘው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ በአሁኑ ወቅትም ከጥቂት ርቀቶች በስተቀር በአብዛኛው የኦሊምፒክ መግቢያ (ሚኒማ) ያሟሉ አትሌቶች ምርጫ በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች አገሪቱን  በዋናነት በመወከል የሚጠቀሰው አትሌቲክስ እንደመሆኑ መጠን የስፖርቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ለወጣት አትሌቶች የውድድር ዕድሎችን መስጠት ትልቁና ዋናው ሥራ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህ መነሻነት ዕድሜያቸው ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣቶች ብሔራዊ ቡድኖችን በማዘጋጀት በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ሲሳተፍ የቆየው አትሌቲክስ ፌዴረሽን፣ ከሁለት ሳምንት በኋላ በፖላንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ዝግጅት ማጠናቀቁንም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት በ400 ሜትር ማሕሌት ፍቅሩ፣ ዝናሽ ተስፋዬና ገዛኸኝ አበሩ፤ በ800 ሜትር ፎዚያ ንጉሴ፣ ባቻ ሞርካ፣ ትዕግሥት ከተማና ታደሰ ለሚ እንዲሁም በ1,500 ሜትር ተሬሳ ቶሎሳ፣ አዳነች አንበሳው፣ ፋንቱ ወርቁና አስረስ ቋዲ ተመርጠዋል፡፡ በ5,000 ሜትር የኔብሎ ቢያዝን፣ ቃልኪዳን ፋንቴ፣ ይታይሽ መኮንን፣ ሰለሞን ቢረጋ፣ ፈትያን ተስፋዬና በየኑ ደገፋ መሆናቸው ሲታወቅ፣ በ3,000 ሜትር ቀጥታ ጌትነት ወሌ በብቸኝነት መመረጡ ታውቋል፡፡

በ3,000 ሜትር መሰናክል ደግሞ አስማረች ነጋ፣ አገሬ በላቸውና ኪዳነማርያም ደሴ ሆነዋል፡፡ በ10,000 ሜትር አምደወርቅ ሞላልኝና ግዛቸው ኃይሉ ሲሆኑ፣ በ10 ኪሎ ሜትር ዕርምጃ የኋላየ በለጠውና ዮሐንስ አራጋው መሆናቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኦቲዝምን ለመቋቋም በጥምረት የቆሙት ማዕከላት

ከኦቲዝም ጋር የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ...

አወዛጋቢው የወልቃይት ጉዳይ

የአማራና ትግራይ ክልሎችን እያወዛገበ ያለው የወልቃይት ጉዳይ ዳግም እየተነሳ...

ተጠባቂው የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የውድድር መለኪያ የሆነው የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በኢትዮጵያ

የሞባይል ገንዘብ ዝውውር የሞባይል ስልክን በመጠቀም ሊገኙ የሚችሉ የፋይናንስ...

የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት...